1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እና ነዋሪዎች አተያይ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 25 2017

አስተያየታውን የሰጡን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከአምና አንጻር ከዘይት እስከ ሽንኩርት፣ ከጤፍ እስከ በርካታ የምግብ ፍጆታ እቃ እና የቤት ውስጥ መገልገያዎች ያልጨመረ ነገር የለም ባይ ናቸው፡

የኢትዮጵያዉያን ዋና ምግብ የሆነዉ የጤፍ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ በመሆኑ ነዋሪዎች መግዛት እየተሳናቸዉ ነዉ
የኢትዮጵያዉያን ዋና ምግብ የሆነዉ የጤፍ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ በመሆኑ ነዋሪዎች መግዛት እየተሳናቸዉ ነዉምስል Seyoum Getu/DW

እየተባባሰ ያለው የኑሮ ውድነት

This browser does not support the audio element.


ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋጋን የማረጋጋት ቀዳሚ ዓላማ ጋር የተጣጣሙ የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሀሳቦችን እንዲሰጥ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ እስካለፈው ህዳር ወር የነበረው እአአ የ2024 የዋጋ ግሽበት በተለይምምግብ ነክ ምርቶች ላይ ከአንድ ዓመት በፊት ከነበው ጋር ሲነጻጸር መረጋጋት ማሳየቱን ጠቁሟል፡፡
ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ግን በዚህ የሚስማሙ አይመስልም፡፡ ከአምና አንጻር ያልጨመረ ነገር የለም ባይ ናቸው፡፡
የኢኮኖሚ  ባለሙያም በሰጡን አስተያየት ጭማሪው በሁሉም ረገድ የተስተዋለ በመሆኑ የመንግስት ወጪን በመቀነስ ግብርናው ላይ አተኩሮ መስራት ምናልባትም የዋጋ መረጋጋቱን ሊያመጣ ይችላል ይላሉ፡፡
አስተያየታውን የሰጡን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከአምና አንጻር ከዘይት እስከ ሽንኩርት፣ከጤፍ እስከ በርካታ የምግብ ፍጆታ እቃ እና የቤት ውስጥ መገልገያዎች ያልጨመረ ነገር የለም ባይ ናቸው፡፡ 
ይህ የሸማቾች አስተያየት ከዋጋ ግሽበት አኳያ ለምን ከሰሞነኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ምልከታ ጋር ተለያየ በሚል አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን፤ “እኔም ሸማች ስለሆንኩ የዋጋ መጨመር ብቻ ነው ሁሌም የምሰማው” የምሉት ባለሙያው፤ ምናልባትም የኮሚቴው ግምገማ ከብር መግዛት አቅም መዳከም ጋር ታይቶ ይሆናል ብለዋል፡፡ መንግስት ወጪውን በመቀነስና የባንኮች በብድር ገንዝብ መርጨትን በጥብቅ በመቆጣጠር የዋጋ ግሽበቱን መቆጣጠሩን ግን ባለሙያው አልሸሸጉም፡፡
ይሁንና ይህም የራሱ የሆነ ጉድለት እንዳለው በመጠቆም፤ “ግን  ደግሞ እዚህ ጋ ኢኮኖሚው ማምረት በሚችለው መጠን ገንዘብ መርጨት ይኖርበታል” ያሉት ባለሙያው “መንግስት እንደ ብሔራዊ ስታትስትክስ እና ፕላን ኮሚሽን ያሉ ተቋማት ተጠቅሞ መረጃ በማሰባሰብ የገንዘብ ፖሊሲ ጥብቅ ቁጥጥርም ሳይዘነጋ ምርት ግን እንዲመረት ገንዘብ ወደ ገቢያ መርጨት” እንዳለበትም መክረዋል፡፡
የፖለቲካል ኢኮኖሚው ባለሙያ አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ስራ አጥነት እና መሰል ፈተናዎች እንዳይደቀኑም ግሽበቱን በተለይም የምግብ ዋጋን ማረጋጋት በሚችሉ በግብርናው ዘርፍ ላይ በማተኮር መስራት አይነተኛ መፍትሄ ነው ሲሉም ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
ሥዩም ጌቱ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ታምራት ዲንሳ
 

አዲስ አበባ ዉስጥ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ አለቅጥ በማሻቀቡ ሸማቾችም ሺያጮችም እያማረሩ ነዉ።ከፍተኛ የዋጋ ንረት ከታየባቸዉ የግብርና ምርቶች አንዱ ሽንኩርት ነዉምስል Eshete Bekele/DW
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW