የዋጋ ግሽበት ቁጥጥር በድሬደዋ እና በሶማሌ ክልል
ሐሙስ፣ ሐምሌ 29 2013![Äthiopien | Dire Diwa | Geschlossene Läden](https://static.dw.com/image/58773603_800.webp)
ማስታወቂያ
የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሀር በአስተዳደሩ የከፋ ሆኗል ያሉትን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር በተወሰደ እርምጃ ከሁለት መቶ በላይ የችርቻሮ መሸጫ ሱቆች እና 11 መጋዘን መታሸጉን ተናግረዋል። በቀጣይ የሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበራትን ከማጠናከር ባለፈ በመሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የመሸጫ ዋጋ ትመና እንደሚደረግም ተናግረዋል።
በነጋዴው ዘንድ በሚታየው የሸቀጥ አላስፈላጊ ክምችት ማድረግ እና በጥቁር ገበያ በሚካሄድ የምንዛሪ ሴራ ለዋጋ ግሽበቱ መባባስ ምክንያት ናቸው ያሉት የሶማሌ ክልል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አህመድ ቦባን በበኩላቸው በዚህ ላይ የክልሉ ካቢኔ ያሳለፈውን ውሳኔ ለዶይቸ ቬለ በስልክ ገልፀዋል። ከቅርብ ቀናት ወዲህ በፍጥነት ተለዋዋጭ በሆነው የሸቀጦች ዋጋ በአብዛኞቹ ላይ ከመቶ በመቶ በላይ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተገለጸው።
መሳይ ተክሉ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ