1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የጤና ተቋማት ጉዳይ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2014

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሁኔታ  ላይ ባለመሆናቸዉ ኅብረተሰቡ ለከፋ ጤና ችግር መጋለጡን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ተናገሩ።

Äthiopien Tigray Konflikt l Plünderung und Zerstörung in Mehal Meda
ምስል፦ Amanuel Sileshi/AFP

ኅብረተሰቡ ለከፋ ጤና ችግር ተጋልጦአል

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሁኔታ  ላይ ባለመሆናቸዉ ኅብረተሰቡ ለከፋ ጤና ችግር መጋለጡን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ተናገሩ። የብሔረሰብ አስተዳደሩ በህወሓት ኃይሎች በተያዘበት ወቅት አካባቢዉ ላi የሚገኙ ሊቀ-ጳጳስ አቡነ ባርናባስ ባደረጉት ጥረት የአካባቢው ሆስፒታል በከፊልም ቢሆን ጉዳት እንዳልደረሰበት ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ አመልክተዋል፡፡
በኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሓት ኃይል በሰቆጣ ከተማ ተደጋጋሚ ወረራ በማድረግ ከፍተኛ የማህበራዊ መስጫ ተቋማት ማውደሙን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለይ በከተመው የሚገኙት 4 ጤና ኬላዎችና አንድ ጤና ጣቢያ መቶ በመቶ መውደማቸውን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አሸብር ግርማ አመልክተዋል። ሥራ የሚያስጀምር ሁኔታ ባለመኖሩ ወደ ስራ መግባት እንዳልተቻለ ደግሞ የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምሩ ቢምረው ተናግረውናል።
ለአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጤና ተቋማት ስራ የሚጀምሩበት ሁኔታ እንዲፈጠር ተጠይቋል ግን ምላሽ ባለመኖሩ ተላላፊና ተላላፊ ያልሁኑ በሽታዎች እንዳይከሰቱ ሰጋት መኖሩን አስረድተዋል። የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርና የምዕራብ ካናዳ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ባርናባስ በጦርነቱ ወቅት ተቋማት እንዳይዘረፉና እንዳይወድሙ ጥረት ማድረጋቸውንና በዚህም መሰረት ሆስፒታሉ የከፋ ጉዳት አልደረሰበትም ብለዋል። በጤና ተቋማቱ ዝርፊያና ውድመት ተሳትፎ አለው ስለተባለው የአገው ብሔራዊ ሸንጎና የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ተቋማቱን ስራ ለማሰጀመር እንቅስቃሴ አላደረገም ስለተባለው ስሞታ አስተያየት ለማካተት ያደረግሁት ጥረት አልተሳካም፡፡

ምስል፦ Amanuel Sileshi/AFP


ዓለምነው መኮንን


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW