1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የውሃ እጥረት የጠናባት ደቡብ አፍሪካ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 6 2012

ደቡብ አፍሪካ ከገጠማት ድርቅ በኋላ ጁሐንስበርግ እና ፕሪቶሪያን በመሳሰሉ ከተሞች ውሐ በራሽን ማደል ጀምራለች። ሌሎች የክፍለ አኅጉሩ አገሮችም ድርቅ ያሳስባቸው ይዟል።

Südafrika Wassermangel |
ምስል፦ Getty Images/AFP/R. Bosch

ትኩረት በአፍሪካ

This browser does not support the audio element.

ደቡብ አፍሪካ ከገጠማት ድርቅ በኋላ ጁሐንስበርግ እና ፕሪቶሪያን በመሳሰሉ ከተሞች ውሐ በራሽን ማደል ጀምራለች። ሌሎች የክፍለ አኅጉሩ አገሮችም ድርቅ ያሳስባቸው ይዟል።

በፕሪቶሪያ ነዋሪዎች ለውሐ እጥረት የዳረጋቸውን ድርቅ ለመመከት እርምጃ የመውሰጃው ጊዜ አሁን ነው የሚል ዕምነት አላቸው። በጉዳዩ አሳሳቢነት የሚስማሙት የደቡብ አፍሪካ የውሐ እና የቤቶች አገልግሎት ምኒስትር ሊንድዌ ሲሱሉ መፍትሔ ለማፈላለግ መንግሥታቸው ከፍተኛ ትኩረት እንደሰጠ አረጋግጠዋል።

ደቡብ አፍሪካውያን በግ ከሚያረቡባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው ካሮ የተባለ ቦታ በውሐ እጥረት ከተጠቁ አንዱ ነው። በዚህ ምክንያት በአካባቢው የሚረቡ በጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። በጎች በውሐ ጥም ለሞት በመዳረጋቸው በገበሬዎች ዘንድ ሥጋት አይሏል። በዛሬው የትኩረት በአፍሪካ መሰናዶ ይልማ ኃይለ ሚካኤል በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውን የውሐ እጥረት እና አልበሽር ገለል ካሉ በኋላ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን በጀመሩት አዲስ ግንኙነት ላይ ያተኩራል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW