1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ምንዛሪ በገበያ እንዲመራ ከተወሰነ ወዲህ ገበያው ምን ይመስላል?

ሰኞ፣ ሐምሌ 29 2016

ጤፍ አዘጋጅቶ፣ ፈጭቶ ለደንበኞቹ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብን ወፍጮ ቤት ባለሙያ "ከ125 አንስቶ እስከ 155 ድረስ እንደሚሸጥ ልዩ ማኛ የሚባል 165 ብር አለ" ብሏል። "170 ብር የሚሸጡ አሉ ይባላል"ብሏል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለይ የአለም አቀፍ በረራ ዋጋ ላይ ጉልህ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።የታክሲና የመድኃኒት ዋጋ ላይ ጭማሪ የለም.።

Äthiopien Addis Abeba | Äthiopischer Aufstieg des Lebensmittels namens „Teff“
ምስል Seyoum Getu/DW

የውጭ ምንዛሪ በገበያ እንዲመራ ከተወሰነ ወዲህ ገበያው ምን ይመስላል?

This browser does not support the audio element.

የውጭ ምንዛሪ ግብይት በገበያው እንዲመራ መወሰኑ ይፋ ከሆነ ፣ ዛሬ ሳምንት ደፈነ።

ከዚህ ውሳኔ በኋላ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን እያወጡ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እኩለ ሌሊት ሊሆን ሲል ጭምር ስለሚቀጥለው ቀን የምንዛሪ ተመን መረጃ ይሰጣል ። በቀን ሁለት ጊዜ የምንዛሪ ተመን ለሕዝብ ይፋ የሚያደርጉ የግል ባንኮችም አሉ። የውጭ ምንዛሪ በገበያ እንዲመራ ከተወሰነ ወዲህ ገበያው ምን ይመስላል? 

ዛሬ ባደረግነው የገበያ ቅኝት ዘይትን የመደበቅ ችግር ስለመስተዋሉ ሸማችም ነጋዴም ከሆኑ አንድ እናት ለመረዳት ችለናል። እኒህ እናት እንዳሉት ሽንኩርትም በስፋት አለ ለማለት ተቸግረዋል። በሌላ በኩል እንግሊዝ ኤምባሲ አካባቢ በተሰማሩበት የባልትና ግብይት ሱቃቸው የተዘጋጀ ሽሮ 300 ብር፣ በርበሬ 600 እንዲሁም አንድ ለምለም እንጀራ 25 ብር እንደሚሸጡ ፣ ጭማሪም አለማድረጋቸውን፣ ሆኖም የተጣለባቸው ግብር ከፍተኛ መሆኑን ነግረውናል። የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል?

የቢራ ዋጋ አልጨመረም። መገናኛ ሾላ ገበያ ውስጥ ያገኘኋቸው ሸማቾች ለመገናኛ ብዙኃን ሀሳብ የመስጠት ፍላጎታቸው ተማጦ መጥፋቱን ገልፀዋል። ቡና፣ እጣን እና መሰል የግብርና ምርቶችን የምትሸጥ ዋጋውን በሚታይ መልኩ በጽሑፍ ያስቀመጠች ሴት ነጋዴ በድምጽ መናገር ባትፈልግም ካለው ሁኔታ አንፃር ያለኝን ከሸጥኩ በኋላ ሥራውን ማቆሜ የማይቀር ነው ብላለች።

የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ገበያ በባህርዳር ከሁለት ዓመት በፊት ምስል Alemnew Mekonnen

 

ኢትዮጵያ ውስጥ ዋነኛ የምግብ ሰብል የሆነው ጤፍ ጭማሪ ታይቶበታል የሚል መረጃ ይደመጣል። ጤፍ አዘጋጅቶ፣ ፈጭቶ ለደንበኞቹ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብን የወፍጮ ቤት ባለሙያ ግብይቱን ጠይቀነዋል። "ከ 125 አንስቶ እስከ 155 ድረስ አለ። ልዩ ማኛ የሚባል 165 ብር አለ" ብሏል። ሆኖም ግን "170 ብር ሁሉ የሚሸጡ አሉ ይባላል" ሲልም የሰማውን ነግሮናል። በኢትዮጵያ ያለው ግጭት፤ የኢኮኖሚ ማሻሻያው አተገባበር ስጋት

የታክሲ እና የመድኃኒት ዋጋ ላይ ጭማሪ የለም

መንግሥት መሠረታዊ የሆኑት የነዳጅ እና የማዳበርያ ሸቆጦች ላይ ድጎማ እንደሚያደርግ አስታውቋል። የከተማው የመደበኛም ይሁን የሜትር የመጓጓዣ - የታክሲ ዋጋ ላይ ምንም የታየ ጭማሪ የለም። ሌላኛው ከውጭ የሚገባው መሠረታዊ ምርት - የመድኃኒት አቅርቦት ላይም የዋጋ ጭማሪ አለመኖሩን ተገንዝበናል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአለም አቀፍ በረራ የቲኬት ዋጋ ላይ ጉልህ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል

 

የሰሞኑን የመንግሥት ውሳኔ ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለይ የአለም አቀፍ በረራ ዋጋ ላይ ጉልህ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። በአየር መንገዱ መተግበሪያ ላይ ማየት እንደሚቻለው ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ ኬንያ እና አስመራ ለደርሶ መልስ ከ32 ሺህ ብር የማይበልጥ የነበረው የቲኬት ዋጋ እጥፍ ጭማሪ ታይቶበታል። የዱባይ የደርሶ መልስ ትኬትን ጨምሮ ቪዛ የሚያስጨርስ የአንድ የጉዞ ወኪል ሠራተኛ ይህንን አገልግሎት ከ 40 ሺህ ባልበለጠ ይሰጥ ነበር ብላለች። ቢበዛ ደግሞ እስከ 48 ሺህ ብር እንደነበር እንዲሁ። አሁን ግን ይህ ዋጋ አሻቅቧል። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-800 አውሮፕላንምስል AP

ገበያውን ለማረጋጋት በመንግሥት ምን እየተደረገ ነው?

 

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር 14 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ለስርጭት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። ሚኒስቴሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ሕገ ወጥ ተግባር ፈፀሙ በተባሉ 2202 የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን በሳምንቱ መጨረሻ አስታውቋል።በኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃው ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተያየት

ባለፈው ሳምንት ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ኢትዮጵያ ውስጥ ከነዳጅ እና ከማዳበርያ ውጪ በብላክ ማርኬት የማይሠራ ምን ነገር አለ?" በማለት የመንገድ ፕሮጀክት ዋጋዎችን ጨምሮ በመደበኛው የባንክ ምንዛሪ ተመን የሚሠራ ምንም ሥራ እንዳልነበር ገልፀው ነበር።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW