1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ሰጪ የግል ተቋማት ፈቃድ ማግኘት

ሐሙስ፣ መስከረም 23 2017

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ "ቢሮዎች" የሥራ ፈቃድ መስጠቱን ይፋ አድርጓል። ፈቃዱን ያገኙት ተቋማት ተቀባይነት ያላቸው የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪ እና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ የማመቻቸት ኃላፊነት ይወጣሉ ተብሏል።

Ethiopien | Addis Abeba
ምስል Solomon Muchie/DW

በውጭ ምንዛሪ ስራ ላይ ለተሰማሩ ተቋማት ፈቃድ መሰጠቱ ያለው አንድምታ

This browser does not support the audio element.

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ሰጪ የግል ተቋማት ፈቃድ ማግኘት 

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ "ቢሮዎች" የሥራ ፈቃድ መስጠቱን ይፋ አድርጓል።

ፈቃዱን ያገኙት ተቋማት ተቀባይነት ያላቸው የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪ እና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ የማመቻቸት ኃላፊነት ይወጣሉ ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የገንዘብ ባለሙያ የተቋማቱ ወደ መስኩ መግባት "የገንዘብ እጥበትን ለመቀነስ፣ የትይዩ ገበያውን እንቅስቃሴ ለማዳከም እና የውጭ ምንዛሪ ግብይቱን ተወዳዳሪ ለማድረግ ያደርጋሉ" ብለዋል።

የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ መመራቱ እና የምሥራቅ ኢትዮጵያ ገበያ

ሌላኛው የዘርፉ ባለሙያ ግን "የወጭ ንግድ እንዲያድግ ከተፈለገ የሀገሪቱ የሰለም ጉዳይ መፈታት እንዳለበት እና የመሬት ባለቤትነት ጉዳይም" ለውጥ እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል። የሀገሪቱ የንግድ ሚዛን ጉድለት የሚስተካከለውም ይህንን መሠረት በማድረግ በሚስፋፋ የሀገር ውስጥ ምርት መሆኑን ለዶቼ ቬለ አመልክተዋል።//

 

ፈቃድ የተሰጣቸው የውጭ ምንዛሪ ሱቆች የተሰጣቸው ኃላፊነት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትናንት መስክረም 22 ቀን 2017 ዓ .ም "የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትን ተደራሽነትን ለማስፋፋትና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማዳበር ያግዛሉ" ላላቸው አምስት ተቋማት የውጭ ምንዛሪ ቢሮ መክፈት የሚያስችል ፈቃድ ሰጥቷቸዋል።

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ሰጪ የግል ተቋማት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል።ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና አንደምታዎች

ተቋማቱ የሚያካሂዱት "የውጭ ምንዛሪ ሽያጭም ሆነ ግዢ ወዲያውኑ የሚፈፀም ብቻ ይሆናል" ተብሏል። እነዚህ ቢሮዎች "ያለ ጉምሩክ ዲክለራሲዮን ከደንበኞች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ የጉምሩክ ፈቃድ ከሚያቀርቡት ደግሞ ከዚያ በላይ የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መግዛት እንደሚችሉ፤ በተጨማሪም "ተፈላጊ የጉዞ  መረጃ ላላቸው የግል ተጓዦች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፤ ለንግድ ሥራ ተጓዦች ደግሞ እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይችላሉ"። 

የዘርፉ ባለሙያዎች አስተያየት 

የምጣኔ ሀብት ተንታኙ አቶ አማንይሁን ረዳ ፈቃዱ የመንግሥት የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እርምጃ ውጤት ቢሆንም የሀገሪቱ የንግድ ሚዛን ጉድለት የሚስተካከለው ግን የሀገር ውስጥ ምርት ሲስፋፋ መሆኑን አመልክተዋል።

ሌላኛው የገንዘብ ባለሙያ  አቶ ኢድሪስ ሰዒድ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎቹ ፈቃድ ማግኘት በጥቂቱ የገንዘብ እጥበትን ለመቀነስ ይረዳሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪን በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሚልኩት ሀብት በዋናነት እንደምታመነጭ የጠቀሱት አቶ አማንይሁን አምራች የሚባሉት ዋና ዋና የሀገሪቱ ክፍሎች የገጠማቸው የፀጥታ እና የሰላም መናጋት ዋናው ለውጭ ንግድ ዕድገት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት መፍትሔ መሆኑን ገልፀዋል በዚያ ላይ ትኩረት ቢደረግ ይበጃል ብለዋል።

የውጭ ምንዛሪ በገበያ እንዲመራ ከተወሰነ ወዲህ ገበያው ምን ይመስላል?

ባንክ ያልሆኑት የውጭ ምንዛሪ ፈቃድ ያገኙት ሱቆች ሥራውን ለማከናወን 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል እና በባንክ በዝግ ተቀማጭ የተደረገ 30 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልጋቸው  ብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ ተገልጿል።  ባንኩ በአሠራሩ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚያደርግም አስታውቋል። 

ባንኩ መንግሥት ያደረገውን የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ተከትሎ በትይዩ ገበያ እና በባንክ መካከል የነበረው የምንዛሪ ተመን ከ 3 በመቶ በታች መውረዱንና ብሔራዊ በንክን ጨምሮ በንግድ በንኮች ያለው የውጭ ምንዛሪ ክምችት ማደጉን ተናግሯል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ 

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW