1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የውጭ ኃይሎች ኮንጎን ለቀዉ ቢወጡ ምን ይከሰት ይሆን?

ቅዳሜ፣ የካቲት 15 2017

ኮንጎ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ውጭ ኃይሎች ሃገሪቷ ዉስጥ ይገኛሉ። እነዚህ ኮንጎ ዉስጥ የተሰማሩት የውጭ ጦር ኃይሎች ሰላም አስከባሪ ፤ የጦር አበጋዝ፤ አማጽያን ኃይሎች፤ የኡጋንዳና የሩዋንዳ የአማጽያን እንዲሁም የኮንጎ መንግስት ኃይላትን ሁሉ የሚያካትቱ ናቸዉ። ኮንጎን ለቀዉ ቢወጡ ምን ይከሰት ይሆን?

የኤም 23 አማፅያን ጎማ ከተማ ኮንጎ
የኤም 23 አማፅያን ጎማ ከተማ ኮንጎ ምስል፦ AFP/Getty Images

የውጭ ኃይሎች-ኮንጎን ለቀዉ ቢወጡ ምን ይከሰት ይሆን?

This browser does not support the audio element.

የውጭ ኃይሎች ሁሉም ኮንጎን ለቀዉ ቢወጡ ምን ይከሰት ይሆን? 
ኮንጎ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ  የተለያዩ ውጭ ኃይሎች ሃገሪቷ ዉስጥ ይገኛሉ። እነዚህ ቦታ ቦታቸዉን ይዘዉ በተለያዩ ዘርፎች ኮንጎ ዉስጥ የተሰማሩት  የውጭ ጦር ኃይሎች ሰላም አስከባሪ ፤ የጦር አበጋዝ፤ አማጽያን ኃይሎች፤ የኡጋንዳና የሩዋንዳ የአማጽያን እንዲሁም  የኮንጎ መንግስት ኃይላትን ሁሉ የሚያካትቱ ናቸዉ።  እነዚህ የተለያዩ የውጭ ኃይሎች ኮንጎ ሪፓብሊክን የውጭ ኃይሎች ሁሉም ኮንጎን ለቀዉ ቢወጡ ምን ይከሰት ይሆን? 
ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በምስራቃዊ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዉስጥ የውጭ ኃይሎች ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። በኮንጎ ለዓመታቶች የዘለቀዉ ማለቂ ያጣዉ ዓመፅ እና ግጭት፤ ከ6 ሚሊዮን በላይ ህዝብን ከገደለ  በኋላ ብዙ ኮንጎውያን በዚህ አመጽ ተዳክመዋል፤ ተስፋቸዉም ተሟጧል። ስለዚህም የፖለቲካ ተንታኝ ፓስካል ሙፔንዳን ጨምሮ የኮንጎ ህዝብ ሃገራቸዉ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እንድታገኝ፤  የዉጭ ኃይላት ሁሉ ሃገሪቱን በፍጥነት ለቀዉ እንዲወጡ ይፈልጋሉ፤ ይመኛሉም።
«በኮንጎ ጦርነት የተሳተፉት ፖል ካጋሜ እና ፤ ሩዋንዳ ላይ ማዕቀብ ሲጣልባቸዉ ማየት እንፈልጋለን።   የተለያዩ ነገሮችን ይዘዉ የሚንቀሳቀሱ አማጺያን  በሙሉ ከኮንጎ ምድር ሲወጡ ማየት እንፈልጋለን።»በኮንጎ ቀውስ የምስራቅና ደቡባዊ አፍርቃ አገር መሪዎች ጉባኤ
ግን ምስራቃዊ ኮንጎ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱት የተለያዩ ወታደራዊ ኃይላት ዴሞክራቲክ ኮንጎን ለቀዉ ቢወጡ ምን ይፈጠር ይሆን?

የኮንጎ ቀዉስምስል፦ Alexis Huguet/AFP

የኮንጎው ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሴኬዲ በኮንጎ ተሰማርቶ የሚገኘዉ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሞንዩስኮ ሀገራቸውን ለቆ እንደሚወጣ ባለፈዉ ዓመት ባካሄዱት የምርጫ ዘመቻ ላይ ቃል-ኪዳን አይነት ነገር ከተናገሩ በኋላ አስከባሪ ኃይሉ ለመዉጣት ሞክሮ ነበር። ይሁን እንጂ በያዝነዉ የጎርጎረሳዉያን 2025 መጀመሪያ፤  በሩዋንዳ በሚደገፈው M 23 የተባለዉ አማጺ ቡድን ፤ በማዕድን የበለጸገውን ምሥራቃዊ ኮንጎ፤ የሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ጎማን ተቆጣጠረ። በመንግሥት ኃይላት ደጋፊዎች የሚታገዘዉ የኮንጎ መንግስት ጦር ኃይል፤ አማጽያኑን ከተማዉ እንዳይገቡ ማስቆም አለመቻላቸዉ፤ መሰረታዊ ችግር መኖሩን የሚጠቁም ነዉ የሚሉት  በለንደን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ፊል  ክላርክ ናቸዉ።
«የኮንጎ አስተዳደር ደካማነት በምስራቅ ሀገሪቱ ያለመረጋጋትም ሆነ የፖለቲካ ክፍተት እንዲፈጥር እና አካባቢዉ በውጭ ኃይሎች እጅ እንዲወድቅ አድርጓል። »

ኤም23 አማጽያንን ማስቆም አይቻልም
የኮንጎ መንግሥት በሩዋንዳ የሚደገፉትን ኤም23 አማጽያንን አይነት ቡድኖች ማስቆም እንደ ስጋት ነው የሚመለከተው። በዚህም ከደቡብ አፍሪቃ የልማት ማህበረሰብ፣ ከተመድ እና ከምስራቅ አፍሪቃ ማህበረሰብ የተውጣጡ የውጭ ወታደሮች ምስራቃዊ ኮንጎን ለማረጋጋት ቢሰማሩም እምብዛም አልተሳካላቸውም። የምሥራቅ አፍሪቃ  ማህበረሰብ ዋና ፀሐፊ ቬሮኒካ ንዱቫ ይህን ያረጋግጣሉ።
«የናይሮቢዉ ሂደት በምስራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ ድጋፉን የዘረጋበት ዋነኛ ዘዴ እንደ አንድ ወንድም  ሆኖ አገልግሏል።    የተደባለቀ ዉጤት ቢኖረዉም ዘላቂ የሆነ መረጋጋትን ማግኘት አንድ ክንውን ሳይሆን ቀስ በቀስ የሚመጣ ሂደት እንደሆነ እንገነዘባለን።» በኮንጎ የሚገኙት የተለያዩ የዉጭ ታጣቂ ኃይላት ኮንጎን ጥለዉ ቢወጡ ምን ይፈጠር ይሆን? ብዙዎች  ይህ ሃሳብ ጥሩ ስለመሆኑ ይጠራጠራሉ። ምክንያቱም እነዚህ የተለያዩ የዉጭ ኃይላት ያለመንግሥት ድጋፍ እራሳቸውን እና ማህበረሰቡን ለመጠበቅ ብሎም ለመከላከል የራሳቸዉ መንገድ የፈጠሩ በመሆናቸዉ ነዉ የሚሉ  ጥቂቶች አይደሉም። ስለዚህም ሁሉም የውጭ ኃይሎች ከዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ለቀዉ ቢወጡ የኮንጎ ህዝብ ሃገሪቱ እንድትረጋጋ እና ሉዓላዊነትዋን እንድታገኝ ካለዉ ከፍተኛ ፍላጎት ይልቅ ሁኔታዉ በኮንጎ  ሁከት የሰፈነበት እና የሥልጣን ክፍፍልን እንደሚያሰፍን አያጠራጥርም።

በኮንጎ ጎማ አየር ማረፊያ አቅራቢያ የተቀሰቀሰ ዉግያ ምስል፦ AP

በኮንጎ ጉዳይ የዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዝምታ ትኩረት በአፍሪቃ፣ የሱዳንና የኮንጎ ጦርነቶች፣ ርዳታና ዲፕሎማሲ
በሩዋንዳ የሚደገፈዉ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ አማፂ ቡድን M23 በቅርቡ በተቆጣጠራቸዉ ከተሞች ዉስጥ ልጆችን ሳይቀር ሰላማዊ ሰዎችን ይበድላል፣ ይገላል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዚሁ ሳምንት መጀመርያ ላይ አሳዉቋል። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ይፋ እንዳደረገዉ አማፂዉ ቡድን የምሥራቃዊ ኮንጎን ትላልቅ ከተሞች ከተቆጣጠረ ወዲህ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀመዉ ጥቃት፣ግፍና በደል እየከፋ ነዉ፤ ብሏል። ታጣቂ ቡድኑ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን በዉትድርና እያሰማራ መሆኑንም አጋልጧል። ቡድኑ ባለፈዉ ሳምንት በሁለተኛ በተቆጣጠራት ቡካቩ ከተማ ዉስጥ ህጻናትን በጅምላ መረሸኑን ዓለም አቀፉ ድርጅት አረጋግጧል።
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር የሩዋንዳ መንግስትና አማፂዉ ቡድን የሰብአዊ መብትንና ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እንዲያከብሩ ቃል አቀባዩ ጠይቀዋል። የምሥራቃዊ ኮንጎን አብዛኛ አካባቢዎች የሚቆጣጠረዉ አማፂ ቡድንን በምትረዳዉ በሩዋንዳ መሪዎች ላይ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጠንካራ ቅጣት እንዲጥል የተለያዩ ወገኖች ቢጠይቁም እስካሁን ሰሚ አላገኙም።


አዜብ ታደሰ  
ኂሩት መለሰ 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW