1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፤ የባሕር በር ጉዳይ

ሐሙስ፣ ጥር 23 2016

በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ጉዳይ አካባቢያዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልገው መግለፁን የተመላከተው የመፍትሔ ሐሳብ ቀድሞውንም የኢትዮጵያ አቋም ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልፀ።

 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለምምስል Solomon Muchie/DW

የውጭ ጉዳይ መግለጫ

This browser does not support the audio element.

በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ጉዳይ አካባቢያዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልገው መግለፁን የተመላከተው የመፍትሔ ሐሳብ ቀድሞውንም የኢትዮጵያ አቋም ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልፀ። 

በስብሰባው የተሳተፈችው ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ የኢኮኖሚ ፣ የአካባቢያዊ ውሕደት እንዲሁም የሰላምና ደህንነት ጉዳይ ነው የሚል አቋም ማንፀባረቋን የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም የስምምነቱን ዝርዝር ሂደት በተመለከተ ከመግለጽ ተቆጥበዋል። 

ኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የሉዓላዊ ግዛቷ አካል አድርጋ ከምትቆጥራት፣ ነገር ግን በራስ ገዝነት ከምትንቀሳቀሰው ሶማሌላንድ ጋር ወታደራዊ እና የንግድ እንቅስቃሴ ለማከናወን የሚያስችላት የባሕር በር ማግኘት የምትችልበትን ስምምነት ታኅሣሥ 22 ቀን 2016 ዓ .ም አዲስ አበባ ውስጥ የተፈራረመች ሲሆን፤ ስምምነቱ ከተፈረመ ከአንድ ወር በኋላ ሂደቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገልጾ ነበር።

ኢትዮጵያ በፀጥታው ምክር ቤት ያራመደችው አቋም


ኢትዮጵያ የባሕር በር ልታገኝ የምትችልበትን የመግባቢያ ስምምነት በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና  በሶማሊላንድፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዱ አዲስ አበባ ውስጥ ከአንድ ወር በፉት በዛሬው ቀን ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ "በሶማሌላንድ ውስጥ የወታደራዊ ሠፈር እና የባሕር መርከብ ሠፈር እንዲኖራት ይፈቅዳል። ክስተቱ ሶማሊያን ክፉኛ ያስቆጣት ሲሆን ጉዳዩን ወደ ተባበሩት ምንግሥታት የፀጥታው ምክር ወስዳው የመወያያ ጉዳይ ሆኗል። ይህንን በተመለከተ ኢትዮጵያ ምን አቋም እንዳራመደች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ተጠይቀዋል። 

የመግባቢያ ስምምነቱ ከተፈረመ ዛሬ አንድ ወር ሞላው

ይህ ስምምነት ከተፈረመ ከአንድ ወር በኋላ ሂደቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገልጾ ነበር። የመግባቢያ ስምምነቱ ከተፈረመ ዛሬ አንድ ወር ሞልቶታል። ገዳዩ ምን ላይ ደረሰ የተባሉት ቃል ዐቀባዩ " የስምምነቱ ዝርዝር ጉዳዮች የሚሠሩ ይሆናል" ካሉ በኋላ ዝርዝሩን መቼ እንደሆን ባይገልፁም ጊዜው ሲደርስ ይገለፃል ብለዋል። ባለፈው ሳምንት ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ ተወካይ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሃመድ ግን  ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት  ለማጠናቀቅ "አሁን ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀር ላይ ነው" ሲሉ ገልፀው ነበር።

የሶማሊላንድ የበርበራ ወደብምስል Brian Inganga/AP/picture alliance

መንግሥት ለግለሰቦች አስተያየት ምላሽ አይሰጥም

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሶማሊያ የባሕር በር በኢትዮጵያም ሆነ በሌላ አካል አይወሰድም በሚል ከሰሞኑ አስተያየት ስለሰጡት ትውልደ ሶማሊያዊት አሜሪካዊት ኢልሃም ኦማር መንግሥት ምን ይል እንደሆን የተጠየቁት ቃል ዐቀባዩ "የግለሰብ አስተያየት ነው" ሀገር ለእንዲህ ያለው አስተያየት ምላሽ አይሰጥም ብለዋል።መንግሥት ከኢትዮጵያ በተለያየ ወቅት ተዘርፈው የወጡ ቅርሶችንና ሐብቶችን ማስመለሱን እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW