1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውዝግብ

ሰለሞን ሙጬ
ሐሙስ፣ ኅዳር 5 2017

አልሸባብ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥጋት እንዳይሆን "በየትኛውም ሁኔታ አሸባሪ ቡድኑን የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል" ሲል ኢትዮጵያ መንግሥስት አስታወቀ። ኢትዮጵያና ሶማሊያ "የማይነጣጠሉ ሕዝቦች እንደመሆናቸው ጊዜያዊ ችግሮችን የመባባስ ፍላጎት የለንም" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውዝግብ - የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰጠዉ መግለጫ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውዝግብ

አልሸባብ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥጋት እንዳይሆን "በየትኛውም ሁኔታ አሸባሪ ቡድኑን የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል" ሲል ኢትዮጵያ መንግሥስት አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠራዊት በአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ውጪ መሆኑን ባለፈው ሳምንት በይፋ ማስታወቋን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም ሲጠየቁ ነው ይህንን ያሉት። ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ "የማይነጣጠሉ ሕዝቦች እንደመሆናቸው ጊዜያዊ ችግሮችን የመባባስ ፍላጎት የለንም" ያሉት ቃል አቀባዩ የሶማሊያ ማንግሥት ይፋ ላራመደው አቋም አልሸባብን እናዳክማለን ከማለት በቀር ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም። 

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተካረረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ እና የራስ ገዟ ሶማሊላንድ [የባሕር በር <-> እውቅና] የመግባቢያ ስምምነት እስካሁን በሂደት ላይ መሆኑ ሲገለጽ በአንድ በኩል፣ አልሸባብን በመዋጋት ለዓመታት የጋራ ግብ እና ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ሆድና ጀርባ አድርጎ ከቃላት ያለፈ የዲፕሎማሲ ቁርቁስ ውስጥ ከቷቸዋል። ይህንን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት የሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ወታደሮች አዲስ በሚዋቀረው የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ውጪ መሆናቸውን በይፋ ማስታወቃቸው ይታወሳል። በዚህ ጉዳይ ላይ ዛሬ የኢትዮጵያን አቋም የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው፣ ለጥያቄው ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም እንዴት እንደሚሆንም ግልጽ ሳያደርጉት ኢትዮጵያ አልሸባብን ማደከሟን ግን ትቀጥልበታለች ብለዋል። ሁለቱ ሀገሮች እንዲህ በሚወዛገቡበት በዚህ ወቅት ሊጠናቀቅ ጥቂት ሳምንታት የቀሩትን የአፍሪካ ሕብረት የሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ (ATMIS)ን በመተካት በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ሚናን ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ የተሳትፎ ጉዳይ ላይ ብያኔ ሰጪው ማን ነው? የሚለው ጥያቄ መሠረታዊ ነው። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው አንድ የዓለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ተንታኝ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል። "ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የምንለው፣ የተባበሩት መንግሥታትን የመሰሉ፣ የአፍሪካ ሕብረትን የመሰሉ ተቋማት እንዲሁምአስተዋጽዖ የሚያደርጉ ሀገራት አስተያየት ይኖራቸዋል።" ይህንን ውዝግብ እንዴት እና ማን ይፈታዋል የሚለውን የተጠየቁት ተንታኙ "ጠንካራ የመንግሥት ተክለ ቁመና ሲኖር ማንኛውም መንግሥት ይሁንታ የመስጠትም የመከልከልም መብት አለው" ብለዋል። የዚህ መነሻ ምክንያቱም ዓለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ኃይል ወደ አንድ ሀገር ሲሰማራ ጉዳዩ ከማዕከላዊ መንግሥት አቅም በላይ ነው የሚል መደምደሚያና ግንዛቤን ታሳቢ ተድርጎ" የሚከናወን በመሄኑ ነው። "በአንድ በኩል ኢትዮጵያን አላሳትፍም ማለት ትችላለች [ሶማሊያ]። በተግባር ሲታይ ግን ይህንን ማለት የሰላም አስከባሪ ኃይሉን ሙሉ ያደርገዋል ዎይ?" ሲሉ ጠይቀዋል። ሶማሊላንድ በዚህ ሁሉ የአካባቢው ውዝግብ ውስጥ ሆናም ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ እውቅናን ከየትኛውም ሀገር ባታገኝም ትናንት አራተኛ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫዋን ስታከናውን ውላለች። የዲፕሎማሲ ተንታኙ በሶማሊያ ለሚሰማራው አዲስ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ እስካሁን በቂ ገንዘብ እና ሀብት ባላገኘበት፣ የሰው ኃይሉ ከውጭ የሚሰባሰብ ሆኖ ሳለ ሰላም አስከባሪን የመምረጡ፣ የመከልከሉም አዝማሚያ እና ውዝግብ በዚህ ወቅት አስፈላጊ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል።

 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW