1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወቅታዊ መግለጫ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 13 2013

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ በሱዳንና ግብፅ ላይ ጫና እንዲያሳርፍ ደብዳቤ መላኳ የአፍሪቃ ሕብረትን ሚና ያከበረ ነው አለች።

Äthiopien Luftbild Grand-Ethiopian-Renaissance-Talsperre
ምስል፦ DW/Negassa Desalegen

«የህዳሴው ግድብ ድርድር፣ የኢትዮ ሱዳን ድንበር ውዝግብ»

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ድርጅት ቢሆንም ለዓለም ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ልማት ከተመድ ጋር በጋራ የሚሰራው የአፍሪቃ ሕብረት በሦስትዮሽ ድርድሩ ላይ መፍትሔ ይሰጣል የሚል ፅኑ እምነት እንዳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። የሱዳን ወታደራዊ ኃይል በወረራ ድንበር ጥሶ የያዘውን የኢትዮጵያ መሬት ለቅቆ እንዲወጣ እና ጉዳዩ በሰላም እንዲፈታ አሁን ድረስ ያልተለወጠ አቋም መያዟም ተገልጿል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በግብፅ ትደገፋለች ባለቻት ሱዳን ከሰሞኑ 61 ኢትዮጵያዊያንን ይዛ መልቀቋን ሚኒስቴሩ አረጋግጧል። በሱዳን ተይዘው ከተለቀቁት 59ኙ ገበሬዎች ፣ ሁለቱ ሚሊሺያዎች መሆናቸውን የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ነገር ግን ሱዳን ጉዳዩን አስመልክቶ 61 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ይዤ ለቅቄያለሁ ማለቷ የተሳሳተ መረጃ ነው ብለዋል።

ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW