1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተባበሩት መንግሥታት ባለስልጣን ስለ ኢትዮጵያ ያወጡትን መግለጫ አጣጣለ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2016

የተመድ ዋና ጸሐፊ የዘር ማጥፋት መከላከል አማካሪ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአራት ክልሎች የዘር ማጥፋትን ጨምሮ የጭካኔ ወንጀሎች እንዳይበራከቱ ከፍተኛ ሥጋት መኖሩን ገልፀው ያወጡት መግለጫ "ኃላፊነት የጎደለው፣ ተገቢ ጥናት ያልተካሄደበት ፣ መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የማይገልጽ ነው" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጣጣለ።

Ambassador Meles Alem
ምስል Solomon Muche/DW

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተባበሩት መንግሥታት ባለስልጣን ስለ ኢትዮጵያ ያወጡትን መግለጫ አጣጣለ


የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ የቴክኒክ ባለሙያዎች ውይይት ጥቅምት 12 እና 13  በግብጽ ካይሮ ይደረጋል
 
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የዘር ማጥፋት መከላከል አማካሪ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአራት ክልሎች የዘር ማጥፋትን ጨምሮ የጭካኔ ወንጀሎች እንዳይበራከቱ ከፍተኛ ሥጋት መኖሩን ገልፀው ሰሞኑን ያወጡት መግለጫ 
"ኃላፊነት የጎደለው፣ ተገቢ ጥናት ያልተካሄደበት እና መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የማይገልጽ ነው" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጣጣለ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተጠይቀው ሲመልሱ ይህንን ሥጋት "በተገቢ ሁኔታ ያልተተነተነ"ብለውታል። 

የኢትዮጵያ ያለፉት ሦስት ወራት የዲፕሎማሲ ሥራ ሥኬታማ ነው ያሉት ቃል ዐቀባዩ በተለይ በሰሜን ኢትትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ከምዕራቡ ዓለም የነበረው የሻከረ ግንኙነት አሁን ተሻሽሎ "ንግግሩም ፣ ቋንቋውም ተለውጧል" ብለዋል። 
ይሁንና ይህ የግንኙነት መሻከር የነበረው ኢትዮጵያ ጦርነት ውስጥ ስልነበረችና ያንን ተከትሎ ይደርስ በነበረው ጉዳት መሆኑ ተጠቅሶ ፣ ሀገሪቱ አሁንም በጦርነት ውስጥ ሆና መንግሥት ይህ ድምዳሜ ላይ እንዴት ሊደርስ ቻለ ? አሁን ያለው ጦርነት በእነዚህ ምዕራባዊያን እይታ ውስጥ አይደለም ወይ? በሚል ለተነሳ ጥያቄ ምላሽ እልሰጡበትም።
የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነትን በተምለከተ የኢትዮጵያን አቋም የተጠየቁት ቃል ዐቀባዩ በኤምባሲው በኩል "ክትትል ይደረጋል" ብለዋል።//

መንግሥት ያጣጣለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ አማካሪ ኢትዮጵያን የተምለከተው መግለጫ ኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት እና ተዛማጅ የጭካኔ ወንጀሎች መንስኤ ሊሆኑ በሚችሉ ችግሮች ውስጥ መሆኗን የሚጠቅስና ዓለም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን የሚጠቁም ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ይህንን ጉዳይ ኃላፊነት የጎደለው ሲሉ ነቅፈው አጣጥለውታል።የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ

የዓለም አቀፍ እርዳታ በቅርቡ ይጀመራል - ተስፋ አለን 

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ 21 ሚሊየን በላይ ዜጎች የእለት ደራሽ የምግብ እርዳታ እንደሚሹ በመንግሥት የታመነ ነው። ጦርነት ያደቀቃቸው አካባቢዎች ደግሞ የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸው ይገለፃል።
ይህንን የተረጂ ቁጥር ጨምሮ ኢትዮጵያ ያስጠለለቻቸው ስደተኞች ከUS እና ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ያገኙት የነበረው የቀልብ እርዳታ መቋረጥ ሰዎች በረሃብ እንዲሞቱ ምክንያት ስለመሆኑ ተዘግባል።
ይህንን በተመለከተ የተጠየቁት ቃለ ዐቀባይ አምባሳደር መለስ በመንግሥት በኩል "የተቋረጠው የእርዳታ አቅርቦት በቅርቡ ይጀመራል" የሚል ተስፋ መኖሩን ገልፀዋል።
የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ መግለጫ በወቅታዊ ጉዳዮች
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከነበረበት ጫና እየወጣ ነውን

ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ በሁለትዮሽም ሆነ በባላ ብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ስኬታማ ግንኙነት አድርጋለች ያሉት አምባሳደር መለስ ከUS ጋር  በኢንቨስትመንት ፣ በንግድና በልማት ትብብር፣ በዲሞክራሲ፣ በፖለቲካና በሰብዓዊ መብት እንዲሁም በመከላከያ እና በፀጥታ ገዳዮች ላይ ጀምራለች ያሉትን በጎ ግንኙነት አስረጂ አድርገው ዘርዝረዋል።
ይህ በአውሮጳ ሕብረትም ሆነ በተናጠል አባል ሀገራቱ እንዲደገም እየተደረገ ነው ያሉትን ጥረት ጠቅሰው አጠቃላይ የሀገሪቱ ከእነዚህ አካላት ጋር በሰሜኑ ጦርነትና ያስከተለው ሁለንተናዊ ቀውስ ምክንያት ሻክሮ የነበረው ግንኙነት አሁን "ንግግሩም፣ ቋንቋውም ተለውጧል" ሲሉ መለወጡን ገልፀዋል።
ከአየርላንድ ጋር የነበረው የግንኙነት መሻከር እየለዘበ መምጣቱ እና በአንድ ወቅት ኤምባሲዎቻቸው ሥጋት ውስጥ የነበሩ ሀገሮች ያ ሁኔታ ተቀይሮ በአሁኑ ወቅት 3 ሀገሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ የመክፈት ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውን በአብነት ጠቅሰዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ
ይሁንና ገጥሞ ለነበረው የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከር መነሻው ምክንያት ጦርነት ከነበረ ኢትዮጵያ አሁንም ኢንተርኔትና ስልክ ያስዘጋ፣ የአስቸካይ ጊዜ ዐዋጅ ያስደነገገ ጦርነት ውስጥ ሆና እንዴት ምዕራባዊያኑ ግንኙነታቸውን ለመሻሸል ያንን መመልከት አልቻሉም ? መንግሥትስ የዲፕሎማሲ ግንኙነቱ ችግር እንዲገጥመው ምክንያት የነበረው ጦርነት በሌላኛው የሀገሪቱ አካባቢ እየቀጠለ ባለበት ከምዕራባዊያኑ ጋር ያለኝ ግንኙነት ተሻሻለ ሲል አይጋጭም ወይ በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም። 

በሌላ በኩል እስራኤል ከሐማስ ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባች ማግስት ኢትዮጵያ ከጎኗ እንድትቆም በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ይህንን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም የተጠየቁት ቃል ዐቀባዩ ክትትል ይደረጋ ከማለት በቀር ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
በሱዳን የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ እስካሁን 33 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው በመግለጫው ተጠቅሷል። በሌላ በኩል የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ የቴክኒክ ባለሙያዎች ውይይት ጥቅምት 12 እና 13  በግብጽ በካይሮ ይደረጋል ተብሏል። ሦስቱ ሀገሮች ከወር በፊት በጉዳዩ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ያደረጉት ውይይት ያለ ስምምነት መበተኑ ይታወሳል።

የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ የቴክኒክ ባለሙያዎች ውይይት ጥቅምት 12 እና 13  በግብጽ በካይሮ ይደረጋል ተብሏል። ምስል Amanuel Sileshi/AFP/Getty Images
ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ በሁለትዮሽም ሆነ በባላ ብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ስኬታማ ግንኙነት አድርጋለች ያሉት አምባሳደር መለስ ከUS ጋር  በኢንቨስትመንት ፣ በንግድና በልማት ትብብር፣ በዲሞክራሲ፣ በፖለቲካና በሰብዓዊ መብት እንዲሁም በመከላከያ እና በፀጥታ ገዳዮች ላይ ጀምራለች ያሉትን በጎ ግንኙነት አስረጂ አድርገው ዘርዝረዋል።ምስል Ethiopian Foreign Ministry
ኢትዮጵያ ውስጥ ከ 21 ሚሊየን በላይ ዜጎች የእለት ደራሽ የምግብ እርዳታ እንደሚሹ በመንግሥት የታመነ ነው። ጦርነት ያደቀቃቸው አካባቢዎች ደግሞ የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸው ይገለፃል።ምስል Eduardo Soteras/AFP
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የዘር ማጥፋት መከላከል አማካሪ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአራት ክልሎች የዘር ማጥፋትን ጨምሮ የጭካኔ ወንጀሎች እንዳይበራከቱ ከፍተኛ ሥጋት መኖሩን ገልፀው ሰሞኑን ያወጡት መግለጫ "ኃላፊነት የጎደለው፣ ተገቢ ጥናት ያልተካሄደበት እና መሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የማይገልጽ ነው" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጣጣለ።ምስል Craig Ruttle/AP/picture alliance
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW