1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሳምንታዊ መግለጫ

ሐሙስ፣ ሰኔ 3 2013

የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ መውጣት መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ምን ያህል ወጡ? ወጥተው የሚያበቁትስ መቼ ነው? ለሚለው ግን ምላሽ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

Äthiopien | Botschafter Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

«የኤርትራ ሠራዊት መውጣት መጀመሩ ተገልጿል»

This browser does not support the audio element.

የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ መውጣት መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ምን ያህል ወጡ? ወጥተው የሚያበቁትስ መቼ ነው? ለሚለው ግን ምላሽ እንደሌላቸው ተናግረዋል። የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሕሩ ኬንያታ የአዲስ አበባ ጉብኝት የሁለቱ ሃገራት የቆየ ጠንካራ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አጋዥ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ የተነጋገሩባቸውን ፍሬ ነገሮች ባይገልፁም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር መምከራቸውንም ተናግረዋል። የትግራይ ክልልን መልሶ የማቋቋም፣ መሠረተ ልማቶችንም የመጠገን ሥራ መጀመሩንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መጀመራቸውንም በመግለጫቸው አውስተዋል።

ሰሎሞን ሙጬ 

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW