1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
እምነትኢትዮጵያ

የዒድ አል ፈጥር በዓል በአዲስ አበባ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 2 2016

1145 ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል ረቡዕ ሚያዝያ 2 ቀን፣ 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በዙሪያው በብሔራዊ ደረጃ ተከብሯል ። በበዓሉ ላይ በርካታ ቁጥር ያለው የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ በመገኘት በጋራ ጸሎት አክብሯል ።

1145 ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል ረቡዕ ሚያዝያ 2 ቀን፣ 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲበር
1145 ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል ረቡዕ ሚያዝያ 2 ቀን፣ 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲበርምስል Solomon Muche/DW

የዒድ አል ፈጥር በዓል አከባበር በአዲስ አበባ

This browser does not support the audio element.

1145 ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል ዛሬ (ረቡዕ ሚያዝያ 2 ቀን፣ 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በዙሪያው በብሔራዊ ደረጃ ተከብሯል ። በበዓሉ ላይ በርካታ ቁጥር ያለው የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ በመገኘት በጋራ ጸሎት አክብሯል ። በክብረ በዓሉ ላይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እንደሚደረገው የሃይማኖቱ መሪዎችም ሆኑ የመንግሥት ተወካዮች በስፍራው ለሚታደመው የሃይማኖቱ ተከታዮች ዛሬ ንግግር ሳያሰሙ ሠላት በመስገድ አክብረውታል ። 

የ1445ኛው ዓመተ ሒጅራ የኢድ አል ፈጥር  የረመዳን ጾም ፍቺ በዓል በብሔራዊ ደረጃ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በዙሪያው ተከብሯል። ካፊያማ በነበረው የማለድልው የዓየር ሁኔታ የሃይማኖቱ ተከታዮች በአዲስ መልክ በታደሰው ስታዲየም እና በዙሪያው በመሰባሰብ የዒድ ሰላትን በጋራ በመስገድ አክብረውታል ።

እስልምና ሃይማኖት ፈጣሪ አንድ መሆኑን ፣ ሰላት መስገድ ግዴታ መሆኑን ፣ ዘካ ማውጣት ፣ የሐጂ ጉዞ ማድረግ እና የረመዳንን ጾም መጾም የሚሉ አምስት አእማዶች አሉት። የኢድ አል ፊጥር በዓል ከአደባባይ የጋራ ስግደትና የጸሎት ሥነ ሥርዓት በኋላ ያለው ለሌለው እያካፈ፤ በመጠያየቅ የሚያከብረው መሆኑን ምእመኑ ተናግረዋል።

ጦርነት ፣ ማንነት ተኮር ጥቃት ያፈናቀላቸው ዜጎች የበዙበት ፣ ድርቅ የሚያስጨንቃቸው የበረከቱበት ፣ የፖለቲካ ውጥረት ያለበት  ኢትዮጵያ የበዓሉ ታዳሚዎች የሰላም ጥሪ እንዲያቀርቡ አድርጓቸዋል። ለክብረ በዓሉ ዝግጅት አድርጎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን የገለፀው ብሔራዊ የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተባለው ኃይል የኢድ አል ፈጥር የሰላት ሥነ -ሥርዓት በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW