1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ቴኳንዶ ማስተሯ ምሕረት ከድር እና የቴኳንዶ ስፖርት

እሑድ፣ የካቲት 6 2014

ወጣት ምህረት ከድር በዎርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ብላክ ቤልት አራተኛ ዳን ማዕረግ ያላት፤ በስፖርቱ እንደ ኢትዮጵያ እጅግ ከተሳካላቸው በጣት ከሚቆጠሩ እንስቶች አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡ በስፖርት የመጀመሪያ ዲግሪዋን በያዘችበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በረዳት መምህርነት የምታገለግለው ምህረት፤ የኢትዮጵያ ቴክዋንዶ ቡድን ምክትል አሰልጣኝም ናት፡፡

Äthiopien | Tekwando | Mihret Kedir
ምስል Seyoum Getu/DW

ከልጅነት እስከ የቴኳንዶ ማስተር የደረሰው የምህረት ከድር የስፖርት ሕይወት

This browser does not support the audio element.

የቴኳንዶ ስፖርትን የተቀላቀለችው ገና የአራት ዓመት ታዳጊ እያለች ነው፡፡ ውልደትና እድገቷ አርሲ ነጌለ ከተማ ሲሆን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በዚያው ተከታትላለች፡፡

ምስል Seyoum Getu/DW

በሴቶች እምብዛም ያልተለመደውን ኃይል መጠቀም የሚመስልና የንኪኪ ስፓርት በሆነው ቴክዋንዶ ስኬታማ ለመሆን ግን ውጣ ውረዱ የህይወት ሰልፉም የዋዛ አልነበረም፡፡

ወጣት ምህረት ከድር በዎርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ብላክ ቤልት አራተኛ ዳን ማዕረግ ያላት፤ በስፖርቱ እንደ ኢትዮጵያ እጅግ ከተሳካላቸው በጣት ከሚቆጠሩ እንስቶች አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡

ምስል Seyoum Getu/DW

በስፖርት የመጀመሪያ ዲግሪዋን በያዘችበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሁን ወቅት በረዳት መምህርነት የምታገለግለው ምህረት፤ የኢትዮጵያ ቴክዋንዶ ቡድን ምክትል አሰልጣኝም ናት፡፡ ባለፈው ክረምት ጃፓን ባዘጋጀችው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይም ተሳታፊ ከነበሩ ልዑክ መሃከል ነበረች፡፡

ምስል Seyoum Getu/DW

ማስተር ምህረት ከድር ስኬታማ በሆነችበት የዎርልድ ቴክዋንዶ እውቅና ከማግኘቷ በፊት በሴትነትም በህይወት ውስጥም ያጋጠሙአትን ብርቱ ፈተናዎች ተፋልማ ያለመችበት ለመድረስ መቻሏንም ታወጋለች፡፡

ሥዩም ጌቱ 

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW