1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ውዝግቦችኢትዮጵያ

የዓለም አቀፉ ቀይመስቀል የመድኃኒት ድጋፍ

ዓለምነው መኮንን
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 1 2018

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከተደረገ ውጊያ በኋላ የከፋ ጉዳት የደረሰባቸውን 16 ቁስለኞች ወደ ሆስፒታሎች ማዘዋወሩን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለጸ። በውጊያው “በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ወይም መቁሰላቸውን” አስታውቋል። የድርጅቱ ሠራተኞች ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች መድኃኒት ያደረሱ ሲሆን በእስር ላይ የሚጎኙትን ጎብኝተዋል።

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አርማ
በሰሜን ወሎ ዞን በነበረ ውጊያ “በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ወይም መቁሰላቸውን” ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

የዓለም አቀፉ ቀይመስቀል የመድኃኒት ድጋፍ

This browser does not support the audio element.

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ትናንት ባሰራጨው ዘገባ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በዞኑ ተባብሶ በቀጠለው ግጭትና ጦርነት ሰባዊና ቁሳዊ ጉዳቶች መድረሳቸውን አመልክቷል፡፡

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በጦርነቱ የቆሰሉ 250 ሰዎችን ማከም የሚያስችል የህክምና መድኃኒት ለወልዲያና ላሊበላ ሆስፒታሎች፣ ሙጃ፣ ኩልመስክና ለሌሎች የጤና ተቋማት ማስራጨቱን ገልጿል፡፡ የቁስለኞችን ማንነት ተቋሙ በመግለጫው አላመለከትም፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ አስተያየት የሰጡን የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ የኮሙዩኒኬሽን ሥራ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ዘውዱ አያሌው፣ 250 ሠዎችን ሊያክም የሚችል መድኃኒት ለጤና ተቋማት ስለመሰጠቱ “ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በሰሜን ወሎ አካባቢ ባለው የግጭት ምክንያት በተለይ ባለፈው ሳምንት ግጭቱ ተባብሶ በመምጣቱ በግጭቱ የቆሰሉ፣ ጉዳት የደረሰባቸው፣ ህክምና የሚፈልጉ ሠዎች መኖራቸውብም ተቋሙ በመረዳቱ የጤና ተቋማትም ቁስለኞችን እየተቀበሉ እንደሚያክሙ ስለታወቀ፣ አስፈላጊ ይህክምና እርዳታ መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ለላሊበላና ወልዲያ ሆስፒታሎች፣ ለሙጃና ኩልሜዳ ጤና ጣቢያዎች 250 ሠዎችን ማከም የሚያስችል መድኃኒት ተሰጥቷል፡” ብለዋል፡፡

የቆሰሉ ወታደሮች ለተሻለ ህክምና እንዲላኩ መደረጉ

ዓለም አቀፉ ይ መስቀል ኮሚቴው በጦርነቱ ወቅት በፋኖ ተይዘው የነበሩ ወታደሮችን መጎብኘት እንደቻለ መግለጫው አመልክቷል፡፡ የጉብኝቱን ዓላማ በተመለምናልባትም ከተ አቶ ዘውዱ እንዳሉት፣ የአያያዛቸውን ሁኔታ መቃኝት፣ የአያያዛቸው ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውንና ከበተሰብ ጋር ለመገናኘት ፍላጎታቸውን ማወቅ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የቆሰሉ ወታደሮች ለተሻለ ህክምና እንዲላኩ መደረጉ አቶ ዘውዱ እንደገለፁልን በፋኖ እጅ የነበሩ 16 የቆሰሉ የመንግሥት የፀጥታ አባላትን ተቋሙ ተቀብሎ የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ ለመንግስት ማስረከቡን ገልፀዋል፡፡

የፋኖ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ከመንግሥት ጋር የሚያደርጉት ውጊያ ከሁለት ዓመት በላይ አስቆጥሯልምስል፦ Mariel Müller/DW

በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሠላም ከተማ ተጠልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካክል በለጋማራ መጠለያ ጣቢያ ይኖሩ ከነበሩ  ተፈናቃዮች መካክል አንዱ ለዶይቼ ቬሌ እንዳሉት በነበረው ጦርነትና አሁንም ባለው ስጋት መጠለያቸውን ለቅቀው በቤተእምነቶች ውስጥ በችግር እንደሚገኙ ገልጠዋል፡፡

በዞኑ በአብዛኛዎቹ ወረዳዎች ሠላሙ እየተሻሻለ ነው መባሉ

በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቱ አሰፋ ተደረገ ስለተባለው የመድኃኒት ድጋፍ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ጠቁመው በዞኑ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ወረዳዎች አሁን በመንግስት ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ መንገዶችም ለትራፊክ ክፍይ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡

ባለፈው ሳምንት የደረሰውን ጉዳት በተመለከት ተጨማሪ አስተያየት እንዲሰጡን ጠይቀናቸው “ጦርነት በመሆኑ ጉዳቶች የኖራሉ” የሚል ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW