የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ቅኝት
ረቡዕ፣ ኅዳር 14 2015ማስታወቂያ
ዓለምን አስጨንቆ የሰነበተው የኮሮና ተሐዋሲ ወረርሽኝ አደናቅፎት የነበረው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ፉክክር ከሦስት ዓመታት በኋላ ዘንድሮ በኳታር መካሄድ ከጀመረ ሦስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። በእነዚህ ቀናትም ባልተገመቱ ሃገራት ቡድኖች አስገራሚ እና ያልተጠበቁ ውጤቶች ታይተዋል። በዛሬው ጨዋታ ጀርመን በጃፓን ቡድን ሁለት ለአንድ መሸነፏ ፣ ሳውድ አረቢያም በእግር ኳሱ ዓለም ከፍተኛ ዝናና እና ታዋቂ ተጨዋቾች ያላት አርጀንቲናን ሁለት ለአንድ ማሸነፏ ሁሉንም ያስደመመ ሆኗል። የሳውዲ መንግሥት የእግር ኳስ ቡድኑን ተጫዋቾች ከወዲሁ በስጦታ እያንበሸበሸ ነው። በሌላ በኩል በዓለም እግር ኳስ ጨዋታ ታሪክ ውስጥ አስተናጋጅ ሀገር ገና በመጀመሪያው ቀን የተሸነፈበት መሆኑም እየተነገረ ነው። አስተናጋጇ ኳታር በኤኳዶር ሁለት ለባዶ በመክፈቻው ዕለት መሸነፏ ተመዝግቧል። በዚህ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ፉክክር የአምስት የአፍሪቃ ሃገራት ቡድኖች ይጫወታሉ። በዛሬው ዕለትም ሞሮኮ ከክሮሺያ ጋር ዜሮ ለዜሮ ተለያይተዋል። ስለዘንድሮው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ፉክክር አስተያየቱን እንዲሰጠን የሃትሪክ የስፖርት ጋዜጣ እንዲሁም ቤስት ስፖርት የተሰኘው የኢንተርኔት ገጽ ባለቤት እና አዘጋጅ የሆነውን ጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ ጠይቄዋለሁ።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ