የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ውድድር
ሰኞ፣ ሰኔ 23 2006ማስታወቂያ
አንድ ተብሎ ዛሬ ሶስተኛው ቀን ግጥሚያ ላይ ደርሰናል ። እስካሁን ኮሎምቢያ ኔዘርላንድስና ኮስታሪካ ወደ ቀጣዩ ጨዋታ አልፈዋል ። የዛሬው ምሽት ውድድር በናይጀሪያና ፈረንሳይ እንዲሁም በጀርመንና በአልጀሪያ መካከል የሚካሄደው ነው።
የዛሬው ውድድር ፤ አፍሪቃውያን ትልቅ ግምት የሚሰጡት ግጥሚያ ነው ። በዚህ በጀርመን ሀገር እጅግ ሰፋ ያለ የመገናኛ ብዙኀን ሽፋን ሲያገኝ የሰነበተውና ዛሬም የተሰጠው ፣ ከናይጀሪያና ፈረንሳይ ግጥሚያ ይልቅ የጀርመንና የአልጀሪያ ውድድር ነው። ጠንካራ ግብ ጠባቂ ፣ ፈጣን የመኻል ሜዳ አከፋፋዮችና አጥቂዎች ያሉት የጀርመን ብሔራዊ ቡድን፤ ከጋና ጋር ካደረገው ግጥሚያ ወዲህ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ፣ ዛሬ ነው ጥንካሬው የሚለካው። አልጀሪያውያን ፤ ከኳስ ፍቅር ችሎታና ድፍረት ጋር እንዴት ይሆን ዝግጅታቸው? በአካባቢያችን ፣ ማለትም በኮሎኝ ኑዋሪ የሆነውን የእግር ኳስ ባለሙያ፣ ክንፈ ወልደ መስቀልን ፣ አነጋግረናል ። ቀጣዩ የስፖርት ዝግጅት ዋነኛ ትኩረት በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ነው ያተኮረውን የዛሬውን የስፖርት ዝግጅት ያቀረበችልን የፓሪስዋ ዘጋቢአችን ሃይማኖት ጥሩነህ ናት።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ
ተክሌ የኋላ
ኂሩት መለሰ