የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ
ሰኞ፣ ሰኔ 9 2006ማስታወቂያ
የስፖርት አፍቃሪዎች በጉጉት ሲጠብቁት የቆዩት የብራዚሉ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ከተጀመረ ዛሬ አምስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል ። በአስተናግጅዋ በብራዚል ድል የተጀመረው ጨዋታ ብዙ የተጠበቀባቸውን የስፓኝን የእንግሊዝን ብሔራዊ ቡድኖች የመሳሰሉ ሽንፈት ታይቶበታል ። ሐምሌ 6 2006 ድረስ የሚቀጥለው የዓለም ዋንጫ ባለድል ማን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ለመገመት የሚያዳግት እየሆነ ነው ። የዛሬው የስፖርት ዝግጅት በዋነኛነት በ20 ኛው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ላይ ያተኩራል ። አትሌቲክስና ቴኒስም በዝግጅቱ ይቃኛሉ ።
ሃና ደምሴ
ሂሩት መለሰ