1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር ማስጠንቀቂያና የመንግሥት ምላሽ

ሰለሞን ሙጬ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 16 2017

የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር (WFP) ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ከአሥር ሚሊዮን በላይ ሰዎች "እየጨመረ የመጣ" ላለው "ርሐብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት" ተጋልጠዋል ብሏላ።

የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር (WFP)
የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር (WFP)

የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር ማስጠንቀቂያና የመንግሥት ምላሽ

This browser does not support the audio element.

የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር በኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ስለሚፈልጉ ሰዎች ላወጣው መግለጫ የመንግሥት ምላሽ 

የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር (WFP) ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ከአሥር ሚሊዮን በላይ ሰዎች «እየጨመረ የመጣ» ላለው «ርሐብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት» ተጋልጠዋል ብሏል።
የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን በዚህ ጉዳይ ላይ ከዶቼ ቬለ ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ «መንግሥት ይህንን ቁጥር አይቀበለውም» ሲል መልሷል።

የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ እንዳሉት የዓለም ምግብ- መርሐ ግብር ይህንን ቁጥር ለማወቅ የት እና መቼ ጥናት እንዳደረገ ግልጽ አለመሆኑን በማንሳት የጥናቱን ተገቢነትም ጥያቄ ውስጥ አስገብተውታል። ኃላፊው አክለውም ድርጅቱ «ከመንግሥት ጋር በጋራ ተነጋግሮ እና ተናቦ የሠራው የጥናት ውጤት ባለመሆኑ መንግሥት ይህንን ለመቀበል ይቸግረዋል» ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትየዓለም የምግብ መርሐ-ግብር (WFP) በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች፣ ቀጠናዊ አለመረጋጋት፣ መፈናቀል፣ ድርቅ እና የኢኮኖሚ ቀውስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በቂ አልሚ ምግብ እንዳያገኙ ማድረጉን፣ «ርሐብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየጨመረ መምጣቱንም» አስታውቋል። 
ድርጅቱ አጋጥሟል ባለው የገንዘብ እጥረት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ጉዳት ለደረሰባቸው 650 ሺህ ሴቶች እና ሕፃናት ያደርግ የነበረውን የተመጣጠነ ምግብ ድጋፍ ለማቋረጥ መገደዱን ገልጿል። አክሎም ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚያከናቸው መሰል ሥራዎቹ ተጨማሪ ገንዘብ በአስቸኳይ ማግኘት ካልቻለ ለ3.6 ሚሊዮን ሰብአዊ ድጋፍ ፈላጊ ሰዎች የሚያቀርበውን የሕይወት አድን የምግብ ድጋፍ በሳምንታት ውስጥ እንደሚያቋረጥ አስጠንቅቋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር (WFP) በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች፣ ቀጠናዊ አለመረጋጋት፣ መፈናቀል፣ ድርቅ እና የኢኮኖሚ ቀውስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በቂ አልሚ ምግብ እንዳያገኙ ማድረጉን ገልጿል።ምስል፦ AP Photo/picture alliance

የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ዓለማየሁ ወጫቶ «እንደ መንግሥት ይህንን ቁጥር ለመቀብል ይቸግረናል» ብለዋል። ኃላፊው አክልው ለዶቼ ቬለ እንደነገሩት ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ሰብአዊ ድጋፍ፣ አስቸኳይም ቢሆን የሚሹት ቁጥሩ እየተጠና በመሆኑ ይሄን ያህል ነው ብሎ መናገር ያስቸግራል ነው ያሉት።
የዓለም ምግብ መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ውስጥ ለርሐብ እና ምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ካላቸው አሥር ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሦስት ሚሊዮን ገደማዎቹ የግጭት እና የከፋ የአየር ንብረት ለውጥ ሰለባዎች ሆነው ከቀያቸው የተፈናቀሉ ስለመሆኑ ጠቅሷል።

በአማራ ክልል እየቀጠለ ያለው የጸጥታ መናጋት የድርጅቱን የሰብአዊ ተግባር እያስተጓጎለ መሆኑን የጠቀሰው ድርጅቱ በዚህም ምክንያት የድርጅቱን በክልሉ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን የመድረስ አቅም አስጊ ማድረጉን አመልክቷል።

የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅቶ ድጋፍ በማቋረጡ የደረሰውን ጉዳት የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ዓለማየሁ ወጫቶ «ጥናት የሚፈልግ ነው» በደመነፍስ እንዲህ ነው ብሎ መናገሩ ለስህተት ይዳርጋል ብለዋል።ምስል፦ Eduardo Soteras/AFP/Getty Images

የተሽከርካሪ ጠለፋ፣ ዛቻ እና ስርቆት ያሉ የወንጀል ተግባራት እየጨመሩ በመሆናቸው በሠራተኞች ደኅንነት ላይ ከባድ አደጋዎችን ያስከትላሉ ያለው የዓለም የምግብ መርሐ-ግብር (WFP) ይህ የሕይወት አድን ዕርዳታ አሰጣጥ ላይ ተፅእኖ አሳድሯልም ብሏል።

የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅቶ ድጋፍ በማቋረጡ የደረሰውን ጉዳት የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ዓለማየሁ ወጫቶ «ጥናት የሚፈልግ ነው» በደመነፍስ እንዲህ ነው ብሎ መናገሩ ለስህተት ይዳርጋል ብለዋል።

ሰብአዊ ድጋፍ በሁለት መልኩ ይቀርባል ያለው የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ድንገተኛ፣ አስቸኳይ እና ጊዜ የማይሰጥ ሲሆን እስከ 72 ሰዓታት የሚሰጥ እና ሌላኛው በዓመት ሁለት ጊዜ በሚደረግ ጥናት ፍተሻ ተደርጎ የሚሠራ ነው ብሏል። መንግሥት በዘላቂነት ርዳታን በራስ አቅም ለመሸፈን አሠራር ዘርግቶ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም የተቋሙ የሥራ ኃላፊ ገልፀዋል።

ሰሎሞን ሙጬ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW