1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የምግብ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ ተወካይ ጥሪ

ማክሰኞ፣ መስከረም 14 2017

በ2024 7.5 ሚሊዮን ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ ወጥነው አብዛኛውን ማሳካታቸውን የገለፁት ኃላፊው ሥራቸው ለሚያስፈልጋቸው ምግብ ማድረስ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ለሥራቸው ትልቁ የፀጥታ ሥጋት ያለበት አካባቢ አማራ ክልል ነው ብለዋል። የችግሩ ደረጃ ይለያይ እንጂ በሌሎች ክልሎችም ይሄው ፈተና የለም ለማለት እንደማይደፍሩ ገልፀዋል።

Äthiopien | WFP | Zlatan Milsic
ምስል Solomon Muchie/DW

የዓለም የምግብ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ ተወካይ ጥሪ

This browser does not support the audio element.

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የሚሰጠው ድጋፍ

ካለፈው ዓመት ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ 8 የረድዔት ሠራተኞች ሕይወት መጥፋቱን እና 20 ያህሉ ደግሞ መታገታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በእንግሊዘኛው ምህጻር WFP አስታወቀ። የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ ፣ በአሁኑ ወቅት ለሥራቸው ትልቁ የፀጥታ ሥጋት ያለበት አካባቢ አማራ ክልል መሆኑን ጠቅሰው ሆኖም ችግሩ ደረጃው ቢለያይም በሌሎች ክልሎችም የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ አይደለም ማለት እንደማይቻል ገልፀዋል።

የሰብአዊነት ሥራ ላይ የሚሳተፉትን ጨምሮ WFP "ሁሉም" ያላቸው አካላት የንፁሃን ዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ አለባቸው ብሏል። ድርጅቱ ትልቅ ፈተናዎች ቢገጥሙትም በዕቅዱ ከያዛቸው ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ ለሚሆኑ ድጋፍ የሚሹ ሰዎች መድረስ መቻሉንም ገልጿል።

«በኮምቦልቻና በደሴ ምግብ ማከፋፈሉ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይቀጥላል«የዓለም የምግብ ድርጅት 

ድርጅቱ የገጠሙት ችግሮች

ከተመደቡ ገና ከአንድ ወር ያልበለጠ ጊዜ የሆናቸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ዝላታን ሚልሲክ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ አደጋ በተለይም በድርቅ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ሰብዓዊ እርዳታ የሚሻ መሆኑን ገልፀው ባለፉት ሦስት ዓመታት ግን ጦርነት እና ግጭት ብሎም ያንን ተከትሎ የተከሰተ የ4 ሚሊዮን እና በላይ ዜጎች የውስጥ መፈናቀል እርዳታ የሚሻውን ሕዝብ ቁጥር ማናሩን ገልፀዋል። 

የዓለም የምግብ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ ተጠሪ ምስል Solomon Muchie/DW

በ2024 ለ 7.5 ሚሊዮን ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ ወጥነው አብዛኛውን ማሳካታቸውን የገለፁት ኃላፊው ሥራችን ለሚያስፈልጋቸው ምግብ ማድረስ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ለሥራቸው ትልቁ የፀጥታ ሥጋት ያለበት አካባቢ አማራ ክልል ነው ብለዋል። ሆኖም ግን የችግሩ ደረጃ ይለያይ እንደሆን እንጂ በሌሎች ክልሎችም ይሄው ፈተና የለም ለማለት እንደማይደፍሩ ገልፀዋል።

አማራ ክልል ውስጥ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ምቹና ሰላማዊ ሁኔታ አለመኖር እንቅፋት ቢሆንም "እርዳታን የማቆም እቅድ የለንም" ብለዋል። የተፈጠረው ሁኔታ ግን በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ አጠቃላይ በሀገሪቱ በጎርጎረሲያን ይሄኛው ዓመት ስምንት የረድዔት ሠራተኞች ሕይወት መጥፋቱን፣ ባለፈው ዓመት ደግሞ 20 ሰዎች መታገታቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል።በትግራይ ክልል የእርዳታ ስርቆትና የእርዳታ መቋረጥ ስጋት

"ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለይም በአማራ ክልል እየጨመረ የመጣው የጸጥታ ችግር ድጋፍ ለሚሹት ለመድረስ እንቅፋት እየሆነብን ነው። ሥራዎቻችን ከፍተኛ የፀጥታ እና የደህንነት ሥጋቶች ያጋጥማቸዋል። በዚህ ዓመት 8 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። እንዲሁም ባለፈው ዓመት 20 በላይ ሠራተኞች ታፍነው ተወስደዋል። ለዓለም ምግብ ፕሮግራም የሰብአዊ ሰራተኞች ደህንነት በጣም አስፈላጊ ነው። እናም የደህንነት ሥጋቶችን ለመቀነስ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በቋሚነት ለማሻሻል ከአጋሮቻችን ጋር እየሰራን ነው። ሁሉም አካላት የሰብአዊነት ሠራተኞችን ጨምሮ የዜጎችን ደህንነት እና ጥበቃ ማረጋገጥ አለባቸው። ያጋጠሙን ትልልቅ ፈተናዎች እንዳሉ ሆኖ ግን WFP 90% በላይ ለተቸገሩት ድጋፍ ፈላጊዎች መድረስ ችሏል ማለት እችላለሁ''

 

የእርዳታ ምግብ ስርቆት

 

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባለፈው ዓመት የእርዳታ ምግብ ስርቆት መከሰቱን በመግለጽ በኢትዮጵያ ይህንን ድጋፍ አቋርጦ ቆይቶ ዳግም ከዓመት በፊት መጀመሩ ይታወሳል።

ይሄው ድርጅቱ የሚሰጠው እርዳታ በታጣቂዎች እና የፀጥታ ኃይላት ይወሰዳል፣ በገበያም ከሀገር ውጪ ጭምር ለሽያጭ ሲቀርብ ይስተዋላል ስለሚባለው ጉዳይ ምላሽ የተጠየቁት ኃላፊው አጥጋቢ ምላሽ ባይሰጡበትም የእርዳታ ምግብ ላልተፈለገ አላማ ሊውል እንደሚችል እና ያንን የተቋሙ ገለልተኛ ያሉት መርማሪ ቡድን ቢገልፀው የተሻለ መሆኑን ገልፀዋል።የዓለም የምግብ ድርጅት ማስጠንቀቂያ

 

"ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ የምግብ ዋስትና እጦት ተዳርገዋል። እያንዣበበ ያለው የላሊና ድርቅ በተለይም በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የከፋ ይሆናል። ወደ 8.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለከባድ የድርቅ አደጋ ተጋላጭ ይሆናሉ ተብሎ የተገመተ ሲሆን ይህም የሚሆነው በቅርብ ጊዜ የምስራቅ አፍሪካ ታሪክ ውስጥ እጅግ የከፋ በሆነው ከ2020 እስከ 23 ድረስ ከተስፋፋው ድርቅ ብዙ ቤተሰቦች ባላገገሙበት ወቅት መሆኑ ነው። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሥራችንን እስከ የካቲት 2025 ለማስቀጠል 341 ሚሊዮን ዶላር ያህል እንፈልጋለን። ያለዚህ ድጋፍ ስደተኞችን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ተጨማሪ የምግብ አቅርቦት ቅነሳ እንዲኖር እና የተመጣጠነ ምግብ እጦት እየተባባሰ እንዲሄድ ያደርጋል"።

የአለም ምግብ ፕሮግራም ከገንዘብ እጥረት ባለፈ የሰላምና የደኅንነት ጉዳይ ለሥራው እንቅፋት መሆኑን እና ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችም ይሁን ኢትዮጵያ ላስጠለለቻቸው የሌሎች ሀገራት ስደተኞች ለመድረስ ፈተና መሆኑን አስታውቋል።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW