የዓባይ ግድብ ውይይት በዋሽንግተን ዛሬ ይጠናቀቃል
ረቡዕ፣ ጥር 6 2012
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የ«ሕዳሴው ግድብ»ን በተመለከተ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የሚያደርጉት ንግግር ዛሬ ይጠናቀቃል። የመፍትኄ ሐሳብም የሚጠበቀው ዛሬ ነው። ሦስቱ ሃገራት በአራት ዙር በሦስቱ ሃገራት መዲናዎች ውስጥ ተገናኝተው በተከታታይ ያደረጉት ንግግር ያለስምምነት ነው የተጠናቀቀው። ዩናይትድ ስቴትስ እና የዓለም ባንክ በተገኙበት ዋሽንግተን ውስጥ የሚከናወነው ስብሰባ የሦስቱ ሃገራት ውጭ ጉዳይ ሚንሥትሮች የተገኙበት ነው። ሦስቱ ሃገራትን ስለሚያወዛግበው የአባይ ግድብ የሚተነትኑ የውኃ እና ውኃ ነክ መሐንዲስ እንዲሁም የማኅበራዊ ሣይንስ ባለሞያን በማነጋገር መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ