የዕርቅና መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴና የዛሬው ችሎት 23 ኅዳር 2006ሰኞ፣ ኅዳር 23 2006በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች፤ አምና ተይዘው የታሠሩትን የዕርቅና መፍትኄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎችና አባላት ለመጎብኘት ወደ ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ከተጓዙ በኋላ ጥቂቶች እሥረኞቹን ለማየት መቻላቸው ተነግሯል።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል Solomon Mengistማስታወቂያ የታሠሩት የኮሚቴ መሪዎችና አባላት በዛሬው ዕለት ጉዳያቸው በችሎት እንደሚታይ ቀነ ቀጠሮ ተይዞ እንደነበረ ቢገለጥም፤ ለታኅሳስ 24 ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ተመልክቷል። ስለዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ የተከሳሾችን የህግ ጠበቃ፤ የህግ ባለሙያ አቶ ተማም አባቡልጉን በስልክ አነጋግረናቸው ነበር። ተክሌ የኋላ ነጋሽ መሃመድ