የዘለቀው የአባይ ንትርክ
እሑድ፣ የካቲት 29 2012
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች የምትገኘው የህዳሴ ግድብ እና የሰነቀችው የወደፊት ዕቅድ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ግድቡን አስመልክቶ ላለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ ሲካሂዱት ቆዩት ውይይት እና ድርድሮች ከሞላ ጎደል ስምምነት የተደረሰባቸው መስለው ኢትዮጵያም ለኃይል ማመንጫነት የተመኘችውን ግድብ ሥራ ስታከናውን ከርማለች። እናም ኢትዮጵያ ግድቡን በውኃ ስለመሙላት ማቀድ መናገር ጀመረች። ከያዝነው ዓመት መጀመሪያ ወራት ወዲህም ግብፅ ሦስተኛ አሸማጋይ ጣልቃ ይግባ የሚል ጥሪዋን አጠናክራ ገፍታበት ዩናይትድ ስቴትስ በጉዳዩ ገባች። (የግብፅ ግፊት ሦስቱ ሃገራት በጎርጎሪዮሳዊው 2015 ዓ,ም የተስማሙበት ውል ይመስላል።) ጉዳዮን ብዙዎች ቢተቹትም ኢትዮጵያም ተቀብላ ተከታታይ ውይይቶች ተደርገው ከስምምነት አልተደረሰም። ታዛቢ ተብላ የቀረበችው ዋሽንግተን ከሰሞኑ በይፋ በጉዳዩ ጣልቃ ገብነት ማሳየቷ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል። የኢትዮጵያ የአባይ ውኃ ተጠቃሚነትና የተካረረው ውዝግብ፣ ወዴት? መውጫውስ? በሚል ዶቼ ቬለ ውይይት አካሂዷል። ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጠቀሙ።
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ