1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዘላቂ ሰላም መፍትሔ እና የግጭት ይቁም ጥሪዎች

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 5 2016

የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ ) ጠየቀ። የመብት ድርጅቱ "የፌደራል መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ኃይሎች እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎችን፣ ከሕግ ውጭ እሥር እና ድብደባዎችን እንዲያስቆም" ጠይቋል።

Logo des Ethiopian Human Rights Council
ምስል Ethiopian Human Rights Council

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጥሪ

This browser does not support the audio element.

የዘላቂ ሰላም መፍትሔ እና የግጭት ይቁም ጥሪዎች 

የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ ) ጠየቀ።

የመብት ድርጅቱ "የፌደራል መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ኃይሎች እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎችን፣ ከሕግ ውጭ እሥር እና ድብደባዎችን እንዲያስቆም" የጠየቀ ሲሆን በድርጊቱ የተሳትፎ ያላቸውን አጥፊዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብም ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በተለይ ባህርዳር በሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ "መንግስት ንፁሃን ዜጎችን ከማንኛውም ዓይነት ጥቃት የመጠበቅ ሕጋዊና መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ" ሲል ጠይቋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ ቦታ የትጥቅ ግጭቶች መቀጠላቸውን ተከትሎ ችግሮች ፖለቲካዊ የሆነ መፍትሔ እንዲፈለግላቸውና በሰላም እንዲፈቱ የሚያሳስቡ ጥሪዎች ከእለት እለት እየተበራከቱ ይገኛል።//

በመራዊው ግጭት ከ80 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ፤ ኢሰመጉ

 

የኢሰመጉ መግለጫ ይዘት

ኢሰመጉ በአማራ ክልል ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ የታጣቁ ኃይሎች ደጋፊዎች ናችሁ በሚል ሰዎችን ከቤታቸው

በመውሰድ ያልታወቀ ቦታ ማሰር እና ያለምንም ፍርድ ግድያ እና ድብደባ እንደሚፈፀም ጠቅሷል። በማሳያነት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ/ም በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ዘንዘልማ ቀበሌ "የታጠቁ ኃይሎች ተባባሪ ናችሁ" በሚል ሁለት ግለሰቦች ከህግ አግባብ ዉጭ ያለምንም ፍርድ በጥይት እንደተገደሉ"፣ በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ሮቢት ቀበሌ "በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጣቁ ኃይሎች ቁስለኞችን አክመሃል" በሚል አንድ የጤና ባለሙያ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደሉን ማረጋገጡን ገልጿል። በክልሉ ከሰሜን ሽዋ አጣዬ እስከ ኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እንዲሁም እስከ ከፍኖተ ሰላም ደረሱ አሉ ያላቸውን አሳሳቢ ግድያዎች፣ እሥሮች እና መሰል ድርጊቶች ዘርዝሮ እርምት ጠይቋል።

አምነስቲ የታሰሩ የኢሰመጉ አባላት እንዲለቀቁ ተጠየቀ

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሁለት አገልጋዮች ከ5 ቤተሰቦቻቸው ጋር የተገደሉበትን፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) የፖለቲካ ዘርፍ ኦፊሰርና ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ በቴ ኡርጌሳን፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በምስራቅ አርሲ የተፈፀሙ ግድያዎችን በማንሳት ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል።

በጋምቤላ ክልል የእርሻ ስራ ላይ የነበሩ 3 የቀን ስራተኞች በታጠቁ ኃይሎች የተፈፀመባቸውን ግድያ የዘረዘረው ኢሰመጉ መንግሥት በፀጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ኃይሎች እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎችን እንዲያስቆም ጠይቋል።

ኢሰመጉ የእስረኞችን አያያዝ ለማየት ፈቃድ ተከለከልኩ አለ

የኢሰመጉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ገመቹን ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀናቸዋል።

የመብት ድርጅቱ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አጣሪ ኮሚቲው በአማራ ክልል በንፁኃን ላይ እየተፈፀመ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ላይ ተገቢው ክትትልና ማጣርት በማድረግ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ የኦሮሚያ ክልል መንግስት በክልሉ በታጣቂ ኃይሎች እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከማውገዝ ባለፈ ስር ነቀል የሆነ ሁሉን አቀፍ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞችን ለሕግ እንዲያቀርብ ጠይቋል።

ግድያ፣ እገታ፣ ቤት መቃጠል እና ዘረፋ - በኦሮሚያ ክልል

እየቀረቡ ያሉ ዘላቂ የሰላም ጥሪዎች 

በባሕርዳር እና የተለያዩ አካባቢዎች በሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን ግድያ አስመልክቶ ሚያዝያ 3 ቀን መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ የሃይማኖት ተከታይ በሆኑ አባቶችና ምዕመናን ላይ ጥቃትና የግፍ ግድያ ፣ እገታና ዝርፊያ እየተፈፀመባቸው ይገኛል" ብሏል። "መንግስት ንፁሃን ዜጎችን ከማንኛውም ዓይነት ጥቃት የመጠበቅ ሕጋዊና መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ" ሲልም ጉባኤው ጥሪ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ ቦታ የትጥቅ ግጭቶች መቀጠላቸውን ተከትሎ ችግሮች ፖለቲካዊ የሆነ መፍትሔ እንዲፈለግላቸውና በሰላም እንዲፈቱ የሚያሳስቡ ጥሪዎች ከእለት ወደ እለት እየተበራከቱ መምጣታቸው አሳሳቢ መሆኑን በመግለጽ መንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈልግ የጠየቁት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬ የወለጋዉ ጥቃትና የኢሰመጉ ጥሪክተር አቶ ያኢይለማርያም "ኢትዮጵያ ዛሬ የገጠማት እጅግ አስፈሪ" ያሉት አደጋ ሊቀለበስ የሚችለው "በሰላምና በሰላም ብቻ ነው።" ብለዋል።

የወለጋዉ ጥቃትና የኢሰመጉ ጥሪ

አክለውም "መንግሥት ከሁሉም አካላት ጋር የሚካሄደውን ግጭት ወደ ሰላም ጠረንጴዛ አምጥቶ ለመደራደር፣ ለመወያየት እና እስከ ሽግግር መንግስት እና ሕገ መንግስትን የማስተካከል ሃሳቦች ድረስ ሊደራደር" ይገባል የሚል ሀሳብ አቅርበዋል።

ኢሰመጉ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ይመጣ ዘንድ በተለያዩ ቦታዎች የሚቀሳቀሱ "ታጣቂ ኃይሎች ሰላማዊ መንገድን በመምረጥ የዜጎች ሰላም እንዲረጋገጥ" የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አድርጓል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW