1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣በአሜሪካውያን ዘንድ ከፍተኛ ጉጉት አሳድሯል

ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2016

ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ፣ ምክትላቸው ካመላ ሃሪስ ወደምርጫ ውድድሩ መግባታቸው የምርጫ ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀየረው ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያዎች ተናግረዋል። የዴሞክራቲክ ፖርቲው ጉባዔ ሲያካሂድ የሰነበተው ብሄራዊ ጉባዔም ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

USA | Nationaler Parteitag der Demokraten (DNC) in Chicago
ምስል Brian Cassella/Chicago Tribune/TNS/via Newscom/picture alliance

ካማላ ሃሪስ እና ዕጩ ምክትላቸው በፓርቲያቸው ጉባኤ ላይ

This browser does not support the audio element.

 

የዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣በአሜሪካውያን ዘንድ ከፍተኛ ጉጉት አሳድሯል

ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን ብቃታቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቶ  ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ፣ምክትላቸው ካመላ ሃሪስ ወደምርጫ ውድድሩ መግባታቸው የምርጫ ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀየረው ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

የዴሞክራቲክ ፖርቲው ጉባዔ ሲያካሂድ የሰነበተው ብሄራዊ ጉባዔም ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በአሜሪካ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ጆ ባይደን በይፋም ባይሆን ፓርቲያቸውን ተሰናበቱ

የአትላንታው ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉ ዘገባ አድርሶናል።

አስቀድሞ ጆሴፍ ባይደን እና ዶናልድ ትራምፕ፣እንደገና በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ተገናኝተው የነበሩ በመሆናቸው ምክንያት የብዙዎችን ትኩረት ተነፍጎ እንዳልነበር ሁሉ፣አሁን ውጤቱ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል፤የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ።

ምርጫው ምን የተለየ ነገር ይዞ መጣ?

ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸውና  በአሜሪካ ነዋሪ የሆኑት የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያው አቶ መኮንን ከተማ፣  የአሜሪካ የዘንድሮ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ ለይት ባለ ሁኔታ የሚታይ እንደሆነ ይናገራሉ።

የጆ ባይደን ከምርጫ ራሳቸዉን ማግለል እና የአፍሪቃዉያን አስተያየት

"መቼም የአሜሪካ ምርጫ ሂደት ለየት ያለ ነው ዛሬ፣ አሁን የምናየው። ሌላ ጊዜ የታወቀ ነው በዚህ በኩል ሪፐብሊካን ዕጩ ዕጩ አለ በሌላ በኩል ዴሞክራቲክ ዕጩ አለ ይባላል።አሁን ለየት የሚያደርገው ምንድነው? እንዳየነው የፕሬዚዳንት ባይደን እወርዳለኹ አሉ። ማን ነው የሚተካቸው እየተባለ ብዙ ሰው ይጠይቅ ነበር። እና አሁን ደግነቱ የተጠበቀው ነው እኔ ጠብቄው ነበር።"

አቶ መኮንን እንደሚሉት፣ በባይደንና ትራምፕ እጩነት ተቀዛቅዞ የነበረው የአሜሪካ መራጮች ስሜት፣ካመላ ሃሪስ ወደ ውድድሩ በመግባታቸው ምክንያት ከፍ ማለት የቻለ ሲሆን፣ምርጫውን ነፍስ እንዲዘራ አድርጎታል።

በባይደንና ትራምፕ እጩነት ተቀዛቅዞ የነበረው የአሜሪካ መራጮች ስሜት፣ካመላ ሃሪስ ወደ ውድድሩ በመግባታቸው ምክንያት ከፍ ማለት የቻለ ሲሆን፣ምርጫውን ነፍስ እንዲዘራ አድርጎታል።ምስል Chip Somodevilla/Getty Images

"አሁን ስሜቱ ከፍ አለ።ባይደን ይሮጣሉ ሲባል፣ሰዉ ቀዝቀዝ ያለ ስሜት ነበረው። አሁን አሁን ከፍ ያለ ስሜት ነው ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ።እኔ የመሰለኝ ደግሞ፣ ፕሬዚዳንት ባይደንን አንድ ሰው ሊገድል ሞክሮ ነበር።በእዛ ምክንያት ደግሞ ሁልጊዜ አሜሪካኖች እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲኾን፣በማዘን እሳቸውን ለመምረጥ ይሞክራል።እና ምንድነው?ይህን ነገር እሳቸው አሸንፈዋል ብለን ስናስብ የላሰብነው ነገር መጣ። ፕሬዚዳንት ባይደን ወረዱ አሁን ምክትል ፕሬዚደንት ሃሪስ ቀርበዋል።እንግዲህ ውጤቱ በጣም ደስ የሚል ነው። እንደዚህ ዐይነት እኔ እውነት ለየት ያለ ነው።የሰሞኑ በጣም ለየት ያለ ነው ብዬ ዐስባለሁ።"

ካማላ ሐሪስ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ ምን አይነት ኤኮኖሚያዊ እንድምታ ይኖረዋል?

 

ምክትል ፕሬዝዳንት ካመላ ሃሪስ  ዛሬ ምሽት ይጠቀቃል ተብሎ በሚጠበቀው የዲሞክራቲክ ፓርቲው ብሄራዊ ጉባዔ፣ፕሬዚዳንታዊ ዕጩነታቸውን በይፋ ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ካመላ ሃሪስ ምክትላቸው እንዲሆኑ የመረጧቸው፣የሚኒሶታው አገረ ገዢ ቲም ዋልዝ፣ትናንት በጉባኤው ሦስተኛ ምሽት የዲሞክራቲክ ፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንትነት ዕጩነታቸውን  በጉባኤዎቹ ፊት ባደረጉት ንግግር መቀበላቸውን አስታውቀዋል።

ካመላ ሃሪስ ምክትላቸው እንዲሆኑ የመረጧቸው፣የሚኒሶታው አገረ ገዢ ቲም ዋልዝ፣ትናንት በጉባኤው ሦስተኛ ምሽት የዲሞክራቲክ ፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንትነት ዕጩነታቸውን  በጉባኤዎቹ ፊት ባደረጉት ንግግር መቀበላቸውን አስታውቀዋል።​​​​​​​ምስል Kamil Krzaczynski/AFP/Getty Images

 

የቀድሞ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ሰዎች ንግግር

በምሽቱ ህዝቡ ለምርጫ የሚቀሰቀስና ከማላ ሃሪስን እንዲመርጥ የሚያነሳሳ ነግግር ፣በተጋባዥ ታዋቂ ሰዎች ተሰምቷል።በቀደመው ምሽት ከተገኙት፣ተናጋሪዎች መኻከል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ ይገኙበታል። ጉባዔውን  በቅርበት የሚከታተሉት የኢኮኖሚ ፖለቲካ ምሁሩ ፕሮፌሰር ተሾመ አበበ ለዶይቸ ቨለ እንደገለጹት፣ የሚሸል ኦባማ ንግግር ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ነው።

በትራምፕ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራና ፖለቲካዊ አንደምታው

"የሚሸል ኦባማ ንግግር ከፍተኛ ጥልቀት የነበረው፣ በአቀራረቡ ግሩም የነበረ፣በአስተሳሰቡ ደግሞ ማንኛውንም ያዳምጠውን ሰው ቀስቃሽ የሆነ ንግግር መቼም በጭራሽ ከአሁን በፊት ያልሰማሁት ዐይነት ስሜት ቀስቃሽ የሆነ ንግግር ነው ያደረገችው"። 

ከፍተኛ ጉጉት ያሳደረው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ምርጫ የሁለት ወራት ገደማ ዕድሜ ቀርተውታል።ምስል Kevin Dietsch/Getty Images

 

የወራት ዕድሜ የቀረውን ምርጫ ማን ሊያሸንፍ ይችላል?

ትራምፕ ላይ የተፈጸመው የግድያ ሙከራ

 

ከፍተኛ ጉጉት ያሳደረው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ምርጫ የሁለት ወራት ገደማ ዕድሜ ቀርተውታል። ለየት ያለ ጠባይ ባለው፣ የሀገሪቱን ምርጫ ፕሬዝደንቱ የሚመረጡት ከፍተኛውን ድምጽ በማግኘት አይደለም። ይልቁንም፣ በየግዛቶቹ አሸናፊው ሁሉንም ይወስዳል በሚባለው ተከታታይ ፉክክር የሚወሰን ነው፤ እነሱ ኤሌክቶራል ኮሌጅ ይሉታል። ጆርጂያን ጨምሮ አንዳንድ ግዛቶች የምርጫውን አሸናፊ ለመለየትወሳኝ ሚና ስላላቸው፣ የሞት ሽረት ፍልሚያ የሚካሄድባቸው ናቸው።

በአሜሪካ ለረጅም ዓመታት ነዋሪ የሆኑት የኢኮኖሚ ፖለቲካ ባለሙያው ፕሮፌሰር ተሾመን ምርጫውን ለማሸነፍ ግምታቸው ለማን እንደሆነ ጠይቅናቸው ነበር።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች ክርክር በአትላንታ

"የኤሌክቶራል ማፑን ሳየው፣በጠቅላላ ድረ ገጹን ሳይ ምናልባት እሷ ተስፋ ይኖራታል። ግን በጣም በጣም ቅርብ ነው የሚሆኑት ሁለቱም ቁጥሩ። አሜሪካን አገር ብዙ በስድሣ በመቶ በሰባ በመቶ የሚያሸንፍ የለም። ምክንያቱም አሜሪካኖች አስተሳሰባቸው ሁሉም በአብዛኛው አንደ ዐይነት ነው። የማይስማሙበት ነገር በጣም ጥቂቶች፣እና ብዙ  ልዩነት የለባቸውም።አንዳንድ ስርነቀል ዐስተሳሰብ ሲመጡ ግን ልዩነት ያመጣል በአራት በአምስት መቶ ታሸንፋለች የሚል ስሜት አለኝ።"ብለዋል።

ታሪኩ ኃይሉ

ታምራት ዲንሳ 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW