1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ እና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች

ዓርብ፣ ነሐሴ 24 2011

ትላንት በዙሪክ  ሲዊዘርላድ  በተካሂደው  የዳይመንድ ሊግ የፍፃሜ ውድድር  ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንደሚያሽንፉ ከፍተኛ ግምት በተሰጠበት  የ5000 ሜትር ወንዶች እና 1500ሜትር ሴቶች  ድል አልቀናቸውም።

Schweiz Leichtathletik Diamond League 2019 Zürich
ምስል DW/H.Tiruneh

«ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውጤት አልቀናቸውም»

This browser does not support the audio element.

 በተለይ የ5000 ሜትር  ውድድሩ ድል ከኢትዮጵያውያ  አትሌቶችም  እጅ እንደማይወጣ ቢገመትም በውድድሩ  ወቅት ተፈጠረ  ባሉት መዘናጋት በበዩጋንዳዊው  አትሌት   ተቀድመው  50ሺ  ዶላርና ልዩ ሽልማት አምልጧቸዋል። በውድድሩ  አትሌት  ሀጎስ ገብረ ሕይወት በሁለተኛነት ሲያጠናቅቅ  ጥላሁን  ኃይሌ  አራተኛ ፤ ሰለሞን በረጋ ደግሞ አምስትኛ  ደረጃ  አግኝተዋል። አትሌቶቹ የዙሪኩ  ስህተት በኳታር አስተናጋጂነት  በሚካሂደው  የአለም  አትሌቲክስ  ሻምፒዮና  ላይ እንዳይደገም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚወስዱም  ከውድድራቸው በኋላ  ለዶቼ ቬለ DW ተናግረዋል። በሴቶች በተካሂደው  የ1500  ሜትር  ፍፃሜ  ውድድር  አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የአራተኛነትን  ደረጃ  አግኝታለች። በስፍራው ተገኝታ ውድድሩን የተከታተለችው ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW