የዛምብያ ምርጫ ውጤት እና ተቃውሞው
ዓርብ፣ ነሐሴ 13 2008ማስታወቂያ
የዛምብያ ምርጫ ውጤት በሀገሪቱ ውዝግብ አስከትሏል ። የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው መሠረት ስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል ።ዋነኛው ተፎካካሪያቸው ሃካይንዴ ሂቻሌማ ውጤቱን ውድቅ በማድረግ ፣ ጉዳዩን በፍርድ ቤት እንዲታይ ፊርማ እያሰባሰቡ ነው ። በአለ ሲመታቸውም በተቃውሞ ምክንያት እንደሚዘገይ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንግ አስታውቀዋል
ፀሐይ ጫኔ
ሸዋዬ ለገሠ