1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምግብ እርዳታ መርሃግብር ለኢትዮጵያውያን ህጻናት እና እናቶች

ሰኞ፣ ሰኔ 22 2012

በኮቪድ-19 እና የምግብ ሰብልን በሚያወድመው የበረሃ አንበጣ ወረርሽኞች መስፋፋት ምክንያት ለከፋ የምግብ እጥረት በተጋለጡ 100 የተለያዩ ወረዳዎች በዝቅተኛ ኖሮ የሚገኙ ዜጎችን በጊዜያዊነት ለመርዳት ድርጅቶቹ በዓመት 35 ሚልዮን ዶላር በጀት መድበው እንቅስቃሴ ጀምረዋል።600 ያህል ትምህርት ቤቶች ችግረኛ ተማሪዎችን የመመገብ ዕቅድ ይከናወናል

Das Logo und der Schriftzug der Hilfsorganisation UNICEF sind am 5. Februar 2008 an der Zentrale in Koeln zu sehen.
ምስል AP

የምግብ እርዳታ መርሃግብር ለኢትዮጵያውያን ህጻናት እና እናቶች

This browser does not support the audio element.

የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም "WFP" በኢትዮጵያ ለከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተጋለጡ ከ 4.5 ሚልዮን ለሚልቁ ሕጻናት ነፍሰጡሮችና አጥቢ እናቶች የሚደግፍ መርሃግብር በጣምራ መጀመራቸውን አስታወቁ:: በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ አስተባባሪ ሚስ አደል ኮደር በተለይ ለዶይቼ ቨለ "DW" እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት በኮቪድ-19 እና የምግብ ሰብልን በሚያወድመው የበረሃ አንበጣ ወረርሽኞች መስፋፋት ምክንያት ለከፋ የምግብ እጥረት በተጋለጡ 100 የተለያዩ ወረዳዎች በዝቅተኛ ኖሮ የሚገኙ ዜጎችን በጊዜያዊነት ለመርዳት ድርጅቶቹ በዓመት 35 ሚልዮን ዶላር በጀት መድበው እንቅስቃሴ ጀምረዋል::ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ውጤታማ እንዲሆኑም  በ 600 ያህል ትምህርት ቤቶች ችግረኛ ተማሪዎችን የመመገብ ዕቅድ ይከናወናል ነው ያሉት ሃላፊዋ:: ዝርዝሩን የፍራንክፈርቱ ወኪላችን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::


እንዳልካቸው ፈቃደ


ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW