1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የዩናይትድ ስቴትስና ቻይና ስምምነት «እመርታ»

ሐሙስ፣ ጥቅምት 20 2018

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና አቻቸው ሺ ጂፒንግ ጋር በቀረጥ እና ምድር ላይ እጅግ ውስን በሆኑ ማለትም (ሬር ኧርዝ) ማዕድናት ላይ አመርቂ ስምምነት ማድረጋቸውን ገለጡ። ደቡብ ኮሪያ ቡሳን ውስጥ የተደረገውን ስምምነት ፕሬዚደንቱ «ጥሩ እመርታ የታየበት» ሲሉ አወድሰዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና አቻቸው ሺ ጂፒንግ ጋር  በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና አቻቸው ሺ ጂፒንግ ጋር በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋልምስል፦ Andrew Harnik/Getty Images

ዶናልድ ትራምፕ ለቻይና ምን ሰጥተው ምን ተቀበሉ?

This browser does not support the audio element.

የዩናይትድ ስቴትስ  ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና አቻቸው ሺ ጂፒንግ ጋር በቀረጥ እና ምድር ላይ እጅግ ውስን በሆኑ ማለትም (ሬር ኧርዝ) ማዕድናት ላይ አመርቂ ስምምነት ማድረጋቸውን ገለጡ ። ደቡብ ኮሪያ ቡሳን ውስጥ የተደረገውን ስምምነት ፕሬዚደንቱ «ጥሩ እመርታ የታየበት» ሲሉ አወድሰዋል ። በስምምነቱ መሰረት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና ላይ ጥለውት የነበረዉን ከፍተኛ ቀረጥ ሊከልሱ መሆናቸውንም ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዛሬ ዘግቧል።

አበበ ሁለቱ አገራት በ«አራት ጉዳዮች ላይ» መስማማታቸውን አብራርቷል ። አንደኛው እና ዋነኛው «በቻይናእና በሌሎች አገራት ላይ አወዛጋቢ የነበረው የቀረጥ ጉዳይ» መሆኑን ጠቅሷል ።

 

ቻይና በበኩሏ እንደ ቦሎቄ፣ አኩሪ አተር፤ ማሽላ የመሳሰሉ የግብርና ምርቶችን ከዩናይትድ ስቴት ገዝታ ወደ አገሯ ለማስገባት መስማማቷ ተዘግቧል ። ከስምምነቶቹ መካከል ፤ ቻይና ፌንቴኒል የሚባለው የኅመም ማስታገሻ ግን ደግሞ እጅግ ሱስ አስያዥ ንጥር ላይ ቁጥጥር ማድረግ እንዳለባትም ተስማምተዋል ተብሏል ።

ቻይና ብራዚል፣ ሩስያ፣ ሕንድ እና ደቡብ አፍሪቃ በጋራ በመሆን አምስቱ አገራት የመሰረቱት «ብሪክስ» የተባለው ቡድን ዋና አባል መስራች ናት ። ከዚህ አንጻር ቻይና ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከብሪክስ ጋር ያላትን ጥቅም አጣጥማ ለማስኬድ ምናልባትም ተግዳሮት ሊገጥማት እንደሚችል አበበ ጠቁሟል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW