1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 5 2015

በዚሁ ጉባዔ የኢትዮጵያ ጉዳይ ቀርቦ ውይይት ሊደረግ ይችል እንደሆን፣ዶይቸ ቨለ ላቀረበላቸው ጥያቄ፣በአሜሪካው ሞርጋን ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሲመልሱ"በዚህ ስብሰባ ላይ አይነሳም።ምክንያቱም ከአጀንዳ ውጭ ነው የሚሆነው።አጀንዳ የተቀረጸለት አለ በዚያ አካባቢ ነው የሚነጋገሩት

USA Washington | US Afrika Gipfel
ምስል፦ Evelyn Hockstein/AP/picture alliance

         

ዩናይትድስቴትስና አፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2014 ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋሽግተን ዉስጥ የተሰየመዉ  ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪቃ ጋር ያላት የፀጥታ፣የንግድ፣የተፈጥሮ ጥበቃና የጤና ትብብርና ግንኙነት በሚጠናከርበት ስልስት ላይ ይመክራል።ይሁንና በዩናይትድ ስቴትሱ ሞርጋን ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ መታፈሪያ እንደሚሉት ጉባኤዉ በተለይ የኢትዮጵያን ግጭት፤ጦርነትና በቅርቡ የተደረገዉን የሰላም ስምምነት አንስቶ ይነጋገራል ተብሎ አይጠበቀም።የአፍሪቃ ሕብረት የቡድን ሐያ አባል እንዲሆን ያቀረበዉን ጥያቄ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት እንደሚደግፉ ከጉባኤዉ በፊት የወጡ ዘገቦች ይጠቁማሉ።የአፍሪቃ መሪዎች  አፍሪቃ በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት መቀመጫ እንዲኖራት የአሜሪካን ድጋፍ ይጠይቃሉ ተብሎ ይገመታል።

ጠቅላይ ማኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሃምሳ ያህል የአፍሪቃ መሪዎች የተገኙበት የአፍሪቃና አሜሪካ መሪዎች ጉባዔ ከትናንት አንስቶ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ እደተካሄደ ነው።ጉባዔው ትናንት በአብዛኛው፣ተጓዳኝ የሆኑ ስብሰባዎችንና ምክክሮችን ሲያስተናግድ የዋለ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን የሚገኙበት ዋናው ጉባዔ ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

 

በዚሁ ጉባዔ የኢትዮጵያ ጉዳይ ቀርቦ ውይይት ሊደረግ ይችል እንደሆን፣ዶይቸ ቨለ ላቀረበላቸው ጥያቄ፣በአሜሪካው ሞርጋን ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሲመልሱ"በዚህ ስብሰባ ላይ አይነሳም።ምክንያቱም ከአጀንዳ ውጭ ነው የሚሆነው።አጀንዳ የተቀረጸለት አለ በዚያ አካባቢ ነው የሚነጋገሩት።ነገር ግን በጎንዮሽ ለአሜሪካ በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እዚህ መኖር ቁልፍ ጉዳይ ነው።አና ባይደን ሁለቱም ተገናኝተው የሚወያዪበት ሁኔታ ይኖራል።መኖርም አለበት ለምሳሌ እንደምገምተው አልሲሲ መጥቷል እና እርሱም ተጽእኖ ለማድረግ ይሞክራል በግድቡ በኩል፤በሌላ በኩል ደግሞ በቅርቡ የሚታዩት ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በዝምታ የሚታለፉ አይደሉም በዚህ ላይ ይነጋገሩሉ።"

የአፍሪቃ ሕብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሴኔጋል ፕሬዝደንት ዋሽግተን ሲገቡምስል፦ Mandel Ngan/AFP/Getty Images

 

የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት በዚሁ ጉባዔ አጋጣሚ በመጠቀም፣ከአሜሪካ አቻዎቻቸው ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ውይይት ማድረግ እንደሚገባቸው ፕሮፌሰር ጌታቸው አመልክተዋል።"ዶክተር ዐቢይን እነማን ናቸው አጅበው የመጡት የሚለው ትኩረት የሚስብ ነው።ምክንያቱም የመከላከያ ሚንስትሩ ከመጣ ከመከላከያ ሚኒስትሩ ጋር ይወያያሉ ማለት ነው።በጎን በኩል እንደዚሁም የኢኮኖሚ ሚኒስትሩ ከመጣ እንደዚሁ ስለኢኮኖሚ ሊነጋገሩ ይችላሉ።"ትናንት ከቀትር በኇላ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሰሜን ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት አፈጻጸምን አስመልክቶ ውይይት አካሄደዋል።የዩናይትድ ስቴትስ አዲስ ሕግ ለኢትዮጵያዉያን

 

ሚስተር ብሊንከን በዚሁ ጊዜ፣የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ አቅርቦትን ለማሻሻል እና አሰፈላጊ አገልግሎቶችን ወደነበረበት ለመመለስ የወሰደውን ዕርምጃ አድንቀዋል።እንዲሁም የሰላም ስምምነቱ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆንና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ታዛቢዎች ግጭት ወደተከሰቱባቸው አካባቢዎች፣ተደራሽነት እንዲኖራቸው አሳስበዋል።ከትግራይ ታጣቂዎች ግጭት መፍታት ጎን ለጎን፣የኤርትራ ኀይሎች ከትግራይ በሚወጡበት ሁኔታ ላይም አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተወያይተዋል።የአፍሪቃ ህብረት የክትትል እና የማረጋገጫ ዘዴን ጨምሮ፣በአፍሪቃ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ለመደገፍ አሜሪካ ቁርጠኛ አቋም እንዳላት፣ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን አረጋግጠዋል።

 

አሜሪካ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በአፍሪቃ የ55 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ፣የጸጥታና የጤና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ማቀዷ፣ከዚሁ ከአፍሪቃና አሜሪካ መሪዎች ጉባዔ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ተገልጿል።የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጌታቸው እንደሚሉትም፣የአፍሪቃ መሪዎች አህጉሪቱ በጸጥታው ምክር ቤት መቀመጫ እንዲኖራት ያቀረቡት ጥያቄ በዚህ ጉባዔ ላይ አንስተው ድጋፍ ሊያገኙም ይገባል።

ምስል፦ Saul Loeb/AFP

"ዋነው መጠቀስ የሚገባው፣ይሆናል ብዬ የማስበው፣የአፍሪቃ ሃገሮች የተባበሩት የዓለም መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ መወከል አለብን ብለዋል።ፕሬዚዳንት ባይደን ያንን ይደግፋሉ ወይ?እሱ እንግዲህ እያንዳንዱ የአፍሪቃ መሪ አጥብቆ ማንሳት ያለበት ነው።እንደአጋጣሚ ሆኖ የአፍሪካ ህብረት ዋና ጸሐፊ አብረው ስለመጡ ይህንን ሁሉ አነጋግረውና አሳምነው ለአፍሪቃ አህጉር አሜሪካ እንድትቆም ያደርጋሉ ብዬ አስባለሁ።"ብለዋል።

 ታሪኩ ኃይሉ 

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW