1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኤኮኖሚሰሜን አሜሪካ

የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ሥራ መዘጋትና መፍትሔዉ

አበበ ፈለቀ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 2 2018

ዉዝግቡ የተነሳዉ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር ያረቀቀዉን በጀት የተቃዋሚዉ የዴሞክራቲክ ፓርቲ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴዎች (ሴናተሮች) አንቀበልም በማለታቸዉ ነበር

የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴዎች በገጠሙት ዉዝግብ ምክንያት ለ41 ቀናት የፌደራሉ መስሪያ ቤቶች ሥራ ተዘግቷል።
በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አብላጫ ድምፅ ያላቸዉ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ጆን ቱኔ ሥለ በጀቱ ዉዝግብ መግለጫ ሲሰጡ።ምስል፦ Kent Nishimura/REUTERS

የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ሥራ መዘጋትና መፍትሔዉ

This browser does not support the audio element.

የዩናይትድ ስቴትስን የፈደራል መንግሥት ሥራን ከ40 ቀናት በላይ የዘጋዉ የበጀት ዉዝግብ የመጀመሪያዉን መሰናክል አልፏል።ዉዝግቡ የተነሳዉ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር ያረቀቀዉን በጀት የተቃዋሚዉ የዴሞክራቲክ ፓርቲ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴዎች (ሴናተሮች) አንቀበልም በማለታቸዉ ነበር።ይሁንና ትናንት የዴሞክራቲኩ ፓርቲ ሴናተሮች በጀቱን በመቀበላቸዉ ረቂቁን በጀት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አፅድቆ ለሕግ መምሪያዉ ምክር ቤት መርቶታል።የሕግ መምሪያዉ ምክር ቤት በጀቱን ለማፅደቅ ድምፅ ይሰጣል።ሥለ በጀቱ ዉዝግብና ምክንያቱ የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW