የአሜሪካንን ጫና የተቃወሙ ሰልፎች በጀርመን ከተሞች
ዓርብ፣ ኅዳር 24 2014ማስታወቂያ
በሦስት የጀርመን ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ምዕራባውያን ሀገራት በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ ታሳድራለች ያሉትን ግፊትና ጫና እንዲሁም ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ያሰራጫሉ ያሏቸውን የሀሰት ዜና በመቃወም ሰላማዊ ሰልፎች አካሄዱ። በዋና ከተማ በርሊን ፣በንግድ ከተማዋ በፍራንክፈርትና የተመድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በሚገኝበት በቦን ከተሞች በተካሄዱት ሰልፎች ላይ የተካፈሉት፣ የኢትዮጵያን ህልውና ይፈታተናል ያሉትን የውጭና የሀገር ውስጥ እንቅስቃሴም ተቃውመዋል። በተለይ ፍራንክፈርት ውስጥ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚያወግዝ ሌላ የአደባባይ ሰልፍ መደረጉን እንዳልካቸው ፈቃደ ዘግቧል።
እንዳልካቸው ፈቃደ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ