የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅትና ጀርመን
ረቡዕ፣ ጥር 7 2006ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የፀጥታ ድርጅት ከሀገር ውጭ በዓለም ዙሪያ፣ በተለያዩ አገሮች፣ 100,000 ያህል ኮምፒዩተሮችን ለስለላ በመትከል ፣ መረጃ መሰብሰብ መቻሉን ኒውዮርክ ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ በትናንቱ እትሙ መግለጹ የሚታወስ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፣ጀርመን ፤ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጸጥታ መረጃ ልውውጥን በተመለከተ አዲስ ስምምነት ለማድረግ የምትሻ ሲሆን ፤ በዚህ ረገድ የወደፊቱ ግንኙነት ምን መሆን እንደሚገባው ፤ የህዝብ እንደራሴዎቿን ም/ቤት ዛሬ አከራክሯል።
የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃ/ሚካኤልን ተክሌ የኋላ በስልክ አነጋግሮታል።
አበበ ፈለቀ
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሃመድ