1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ውዝግብ

ሐሙስ፣ ኅዳር 4 2012

በዩናይትድ ስቴትስ በቀጠለው የፖለቲካ ሽኩቻ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣናቸውን ለግል  መጠቀም እና አለመጠቀማቸውን ለማጣራት የእማኝነት ቃል በይፋ መሰማት ተጀመረ።

USA Impeachment öffentliche Anhörung
ምስል AFP/O. Doulliery

«ጉዳዩን ያውቃሉ በተባሉ ላይ ምርመራው በይፋ ተጀምሯል»

This browser does not support the audio element.

በጎርጎሪዮሳዊው 2020ዓ,ም በሚካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በእጩነት ሊቀርቡ ይችላሉ ተብለው የተገመቱት የቀድሞው የቀድሞው ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደንን ለማስተቸት ልጃቸውን በዩክሬን የሙስና ማጣራት ክስ እንዲመሰረትባቸው ፕሬዝደንት ትራምፕ የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ጠይቀዋል በሚል ነበር ሲተቹ የቆዩት። ትችቱንም ተከትሎ ለሳምንታት የእማኞች ድምፅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቻ ሲቀርብ ነበር። ከትናንት ጀምሮ ደግሞ በይፋ በመገናኛ ብዙሃን ለሕዝብ መሰማት ጀምሯል። ይህ የተፈለገው የሕዝቡን ትኩረት ለመሳብ እና ተፅዕኖ ለማሳደር መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ ኢትዮጵያዊ የሕግ ባለሙያ ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ፕሬዝደንት ትራምፕ የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ኤርዶ ኻንን በቤተ መንግሥታቸው ተቀብለዋል። ዝርዝር ዘገባ ከዋሽንግተን ዲሲ መክብብ ሸዋ ልኮልናል። 

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW