የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች ክርክር
ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2001ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በያዝነዉ ወር ማብቂያ ለሚደረገዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚፎከከሩት የሐገሪቱ ሁለት ተቀናቃኝ ፓርቲዎች እጩዎች ትናንት የመጨረሻዉን የፊት ለፊት ክርርክር አድርገዋል።በሥልጣን ላይ ያለዉ የሪፐብሊካኖቹ ፓርቲ እጩ ሴናተር መኬይንና የተቃዋሚዉ የዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ሴናተር ባራክ ኦባማ ለሰወስተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጉት ክርክር ከቀዳሚዎቹ ሁለቱ ብዙ የተሟሟቀና አንዱ ሌላዉን በጠንካራ ቃላት የተቸበት ነዉ።ባብዛኛዉ በምጣኔ ሐብት ላይ ባተኮረዉ ክርክር ኦባማ ከመኬይን የተሻለ ነጥብ አግኝተዋል።ነጋሽ መሐመድ የዜና መልዕክቶችን አሰባስቧል።