የዩኤስ ምርጫ ለአውሮጳውያን አንደምታው፦ ቃለ መጠይቅ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26 2017ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ አገር አቀፍ ምርጫ ዛሬ እየተከናወነ ነው ። የቀድሞው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕን አለያም ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሐሪስን የወደፊቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት አድርጎ ለመምረጥ አሜሪካኖች ድምፅ እየሰጡ ነው። ይህን የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ አውሮጳውያን እንዲህ በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተሉት ለምን ይሆን? ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ ያነጋገርሁት የብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ጥያቄውን በማብራራት ይጀምራል ።
በዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚደንትነት ዘመን አውሮጳ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የነበራት ግንኙነት በጆ ባይደን ጊዜ እንዳለው አይደለም ። እንደውም ዶናልድ ትራምፕ በአንድ ወቅት አውሮጳዎች ለሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት፦ ኔቶ መክፈል አለባቸውም ሲሉ ነበር ። ኔቶ ከሩስያ ጋር የገባው ቅራኔ እና ፍጥጫ የሚታወቅ ነው ። ይህን ሁሉ ጊዜ አውሮጳዎች ለምን በደንብ ሳይዘጋጁ ቀሩ?
የአውሮጳ ሃገራት መሪዎች በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ማን ቢያሸንፍ ይፈልጋሉ? ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል ።
ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ