1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩክሬን ደም አፋሳሽ ጦርነት በዓለም የኃይል አሰላለፍ ላይ ምን ያስከትላል?

እሑድ፣ የካቲት 27 2014

በዩክሬን ጦርነት የጀመረችው ሩሲያ ብርቱ ማዕቀቦች ቢጣሉባትም እስካሁን አላፈገፈገችም። በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉበት የሚገመተው እና በርካቶችን ለመፈናቀልና ለስደት የዳረገው የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ አስራ አንድ ቀናት ተቆጠሩ። ይኸ ጦርነት እየፈጠረ ካለው ሰብዓዊ ቀውስና ውድመት ባለፈ በዓለም የኃይል አሰላለፍ ምን ያስከትላል?

Insignien und die Macht der Bildsprache

እንወያይ፦ የዩክሬን ደም አፋሳሽ ጦርነት በዓለም የኃይል አሰላለፍ ላይ ምን ያስከትላል?

This browser does not support the audio element.

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (NATO) አሜሪካ፣ ካናዳ እና በርካታ የአውሮፓ አገራት በጎርጎሮሳዊው 1949 ያቋቋሙት እና 30 አባላት ያሉት ወታደራዊ ኅብረት ነው። አገራቱ ከቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት የነበረባቸውን የጸጥታ ሥጋት በጥምረት ለመመከት ኔቶ ሲቋቋም አባላቱ አስራ ሁለት የነበሩ ሲሆን ቀሪዎቹ የተቀላቀሉት እስከ 2020 ባሉት አመታት በሒደት ነው። 

የኔቶ አባልነት የተመሠረተበትን "ሥምምነት መርኆዎች ለማራመድ እና ለሰሜን አትላንቲክ አካባቢ ጸጥታ የበኩሉን አስተዋጽዖ ለሚያበረክት የአውሮፓ አገር ሁሉ ክፍት ነው።" ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (NATO) አባል ባትሆንም የጠበቀ ግንኙነት ነበራት። የሩሲያው ፕሬዝደንት ኔቶን እንደ ሥጋት የሚመለከቱ ሲሆን ዩክሬን አባል የመሆን ዕድሏን ባለፈው የካቲት 17 ቀን 2014 ለጀመሩት ወረራ በምክንያትነት አቅርበዋል። 

ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የዩክሬን ከተሞች ከምድር፣ ከሰማይ እና ከባሕር በሚምዘገዘጉ የሩሲያ መሣሪያዎች ሲደበደቡ አስራ አንድ ቀናት ተቆጥረዋል። በውጊያው በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች እና ወታደሮች እንደተገደሉ ይገመታል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ መሠረት እስከ አርብ የካቲት 25 ቀን 2014 ድረስ ብቻ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናውያን አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል። ከእነዚህ መካከል ግማሽ ሚሊዮን ያክሉ ወጣቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ይገምታል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ከፍተኛ ኮሚሽን በበኩሉ ተገን እና እርዳታ የሚፈልጉ ዩክሬናውያን ቁጥር በሒደት ከአራት ሚሊዮን ሊልቅ እንደሚችል ይፋ አድርጓል። 

አሜሪካ፣ ኔቶ እና የአውሮፓ አገራት በቀጥታ በጦርነቱ ባይሳተፉም ዩክሬንን በማገዝ ላይ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ በሩሲያ ላይ ብርቱ ማዕቀቦች በተደጋጋሚ እየጣሉ ናቸው። 

የዛሬው የውይይት መሰናዶ ይኸ ጦርነት ሊያስከትል በሚችለው ዳፋ እና በዓለም የኃይል አሰላለፍ ላይ የሚኖረው አንድምታ ላይ ያተኮረ ነው። በውይይቱ የሕግ ባለሙያ እና የፖለቲካ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ፤ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች ገበያው ንጉሴ ከብራስልስ እንዲሁም አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ተሳትፈዋል። 

ውይይቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW