የዩክሬይን የፓርላማ ምርጫ ዉጤትና እንደምታዉ
ሰኞ፣ ጥቅምት 17 2007ማስታወቂያ
በዩክሬይኑ ለ450 የምክር ቤት መንበሮች ነበር ዕጩዎች የተወዳደሩ ሲሆን ሩስያ የጠቀለለቻት የክሪም ማለትም የክሪሚያግዛት እና በመፍቀሬ ሩስያ የተያዘዉ የምስራቅ ዩክሬይን ተወካዮች መቀመጫ ሳይያዙ እንደሚቆዩ ተመልክቶአል። በምስራቅ ዩክሬይን የሚገኙት መፍቀረ ሩስያ ተገንጣዮች በበኩላቸዉ ለጥቅምት 23 ምርጫ እንደሚያካሂዱ ገልጸዋል። ተገንጣዩቹ የጠሩት ምርጫ ግን በአዉሮጳዉ ህብረት ተቀባይነትን አላገኘም። በዩክሬይን ምርጫ ዉጤት የአዉሮጳ መንግሥታት አመለካከት ምን ይመስላል? ምንም እንኳ በዩክሬዩን የፓርላማ ምርጫ ቢካሄድም የምስራቅ ዩክሬይን ዉዝግብ አሁንም አለመፈታቱ የታወቀ ነዉ። ይህ ምርጫ ለዉዝግቡ መፍትሄ ያመጣ ይሆን? ዩክሬይን ከሩስያ ጋር ግንኙነት ላቋርጥ ብትል ሁኔታዉ የከፋ እንደሚሆን የአብዛኞች አመለካከት ነዉ ። የምስራቅ ዩክሬይን መፍቀሬ ሩስያንን ትረዳለች የምትባለዉ ሩስያ ከዩክሬይኑ የፓርላማ ምርጫ በኋላ፤ የሁለቱ ሃገራት የኤኮነሚ ግንኙነትስ በምን አይነት ይቀጥል ይሆን? የብራስልሱን ወኪላችን በስልክ አነጋግረነዉ ነበር።
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ