የዪናይትድ ስቴትስ እና ቻይና ግንኙነት
ረቡዕ፣ የካቲት 10 2002ፕሪዝደንት ኦባማ ባንጻሩ ከመንፈሳዊዉ መሪ ጋር ተገናኝተዉ ስለሚያደርጉት ገንቢ ውይይት ከወዲሁ እንዳስደሰታቸዉ የዋይት ሃዉሱ ቃል አቀባይ መግለጹ ይታወቃል። ምንም እንኻ ፔኪንግ ቅሪቃዋን አሳይታ ዛቻን ብታሰማም ለፕሪዝደንት ኦባማ የመንፈሳዊዉን መሪ ዳላይላማን ተቀብሎ ማነጋገር የዛሪ ዋንና መረሃ-ግብራቸዉ ነዉ። የዶቸ ቬለዋ Christina Bergmann በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ስላለዉ ግንኙነት የዘገበችዉን አዜብ ታደሰ እንዲህ አጠናቅራዋለች።
የአሜሪካዉ ፕሪዝደንት ባራክ ኦባማ በምረጡኝ ዘመቻ ፕሮጋንዳቸዉ ከአገሪቷ የቀድሞዉ ፕሪዝደንት ከቡሽ የተለየ እና የተሻለ ሁኔታን ለአገራቸዉ እንደሚያመጡ በተለይ ለቻይና የአሜሪካንን ጠንካራ ጎን እንደሚያሳዩ ነበር ቃል የገቡት። ኦባማ የፕሪዝደንትነት ስልጣንን ከያዙ በኳላ ያ ሁሉ ፉከራ ሳይሳካ አለምን የመታዉ የምጣኔ ሃብት ችግርን በተመለከተ፣ አሜሪካና ቻያና የአገሮቻቸዉን ዋና ዋና ተጠሪዎች በመያዝ ሁለቱ የመንግስታት መሪዎች ጉባኤ ተቀምጠዉ ነበር። በስተ መጨረሻ ግን አሜሪካ የቻይና አምስት መቶ ቢሊዮን በላይ እዳ እንዳለባት ነዉ ግልጽ የሆነዉ። የአሜሪካዋ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ህላሪ ክሊንተን ስልጣናቸዉን እንደያዙ ፔኪንግን ነበር ለመጀመርያ የጎበኙት። ትኩረትና እና ዉይይታችን ሁለቱ አገሮች ዋንና እና አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ላይ እንጂ በቻይና የሰብአዊ መብት ይከበር እያልን አንነታረክም ሲሉ መግለጻቸዉ ይታወሳል። ሚኒስትሯ በዚህ ንግግራቸዉ በርካታ ነቀፊታ ደርሶባቸዋል።
ባራክም ቢሆኑ ባለፈዉ አመት ከዳይላላማ ጋር ለመገናኘት የቀረበላቸዉን ግብዣ ባለመቀበላቸዉ ትልቅ ነቀፊታን ተቀብለዋል። ከዝያም የቻይና የመጀመርያ ጉብኛቸዉ በቻይና መንግስት ፍላጎት በሸንጋይ ካሉዉ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ባደረጉት ጉብኝት ባሰሙት ንግግር
«ከቻይና ጋር አንገብጋቢ በሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ባለ ሁኔታ ተነጋግረናል። ኢኮነሚ እንዲያሰራራ፣ ጥራት ያለዉ የሃይል ምንጭ ለመገንባት፣ ስለ ኒኩሊየር ሃይን ቅነሳ፣ ስለ ከባቢ አየር ክብካቤ፣ እንዲሁም በእስያ እና በአለም ዙርያ ስላለዉ ሰላም እና የአካባቢ ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ነዉ ትኩረታችንን ያደረግነዉ»
የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ገጽታ አሁን ቀየር ያለ ይመስላል። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ህላሪ ክሊንተን በቅርቡ ፓሪስ ላይ ባሰሙት ንግግር ኢራን ላይ ይደረግ ስለተባለዉ እቀባ፣ ቻይናም ስምምነቷን ማሳየት አለባት፣ አለበለዝያ ከቻይና ጋር ያለንን የዲፕሎማሲም ሆነ የኢኮነሚ ግንኙነት መቀነስ አለብን ሲሉ ገልጸዋል። ህላሪ ክሊንተን የአለም አቀፉ የኢንተርኔት መረጃ መፈለግያ መርሃ ግብር ማለት Googl ቻይና እያደረሰችበት ቀዉስ እንድትታቀብ ሲሉ ቀደም ሲል ገልጸዋል። በተጨማሪ ዩናይትድ ስቴትስ 6,4 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሳርያ ለታይዋን መሸጣን ማስታወቅዋ የቅርብ ግዜ ከት ነዉ። ከዚህ ቻይናን ከሚያስከፋ ድርጊት በኻላ ደግሞ ባራክ ኦባማ ለትቤት ተለቅ ያለ የራስ ገዝ እንዲሰጥ ከሚታገሉት ከትቤቱ መሪ ከዳላይላማ ጋር ለመገናኘት በደስታ ዝግጅት ላይ መሆናቸዉ ህዝባዊት ቻይናን ክፉኛ አስቆጥቶአል። ስለ ቻይና የፖለቲካ ሁኔታ አዋቂዋ Nina Hachigian የግዜ ጉዳይ ሆኖ ነዉ እንጂ ቀድሞዉኑ ይህ ሁሉ እንደሚመጣ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነዉ። የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት ዉስብስብ እና እጅግ ልዪነት የሚታይበት ነዉ ባይ ናቸዉ።
«ባለፈዉ አመት መጨረሻ ላይ አሜሪካዉያን ቻይናን ያስቆጣ ዉሳኔዎችን አሳልፈዋል። ለምሳሌ ፕሪዝደንት ኦባማ ቻይና ለሽያጭ አገራቸዉ ለምታስገባዉ የመኪና ጎማ በህዝባቸዉ ፍላጎት መሰረት ቀረጥ ጨምረዉ እንዲከፍሉ ዉሳኔ ማስተላለፋቸዉ ነዉ»
ስለዚህም ይላሉ የቻይና ፖለቲካ ተንታኝዋ Nina Hachigian ኦባማ በቻይና ፖለቲካቸዉ ስኬታማ ናቸዉ ባይናት ይኸዉም የኮፐን ሃገኑ የከባቢ አየር ሁኔታ ጉባኤ ስኬታማ ነዉ ባይባልም ቻይና ታደርጋለች ተብሎ ያልተጠበቀ ጉዳይን ፈጽማለች። ቻይና የአለም አቀፉ የአቶም መቆጣጠርያ ቢሮ በኢራን ላይ ለሚደረገዉ እቀባ ትብብርን ላለማድረግ ብታፈገፍግም፣ ሰሜን ኮርያ ላይ የተጣለዉን እቀባ ላይ ተባብራለች። ይህን አይነት ትብብር ቀደም ሲል አላሳየችም። በሌላ በኩል በአለማችን የደረሰዉ የፊናንስ ቀዉስን በተመለከተ ከሌሎች አገራት ጋር ያላትን ምጣኔ ሃብት በማዉጣት ቀዉሱን ለማስተካከል ሞክራለች። ይህ ደግሞ ዩኤስ አሜሪካ የምትሻዉ ነበር።
ቻይና ምንም እንኻ አሜሪካ የምትሻዉን አንዳንድ ጉዳዮች ባለፉት አመታት እያሟላች ብትሄድም የትቤት እና የታይዋን ጉዳይ ሲነሳ ቻይናን እንዲህ ማስቆጣቱ የሚያስደንቅ አይደልም ይላሉ የቻይና ፖለቲካ ተንታኝዋ
«በርግጥ ቻይናን አስቆጥቶአል፣ ሁኔታዉ ግን ካለፉት አመታት ጋር ሲነጻር የዘንድሮዉ ቁጣ ለስለስ ያለ ነዉ። ቻይና ይህን ያህል ቁጣዋ እንደምታሰማም የታወቀ ነበር»
ለወደፊትም ይላሉ በአሜሪካ እና ቻይና መካከል ያለዉ ሁኔታ እየተሻለ ይመጣል ብለዉ ያምናሉ። በርካታ የቻይና የፖለቲካ ተንታኞች ግን ባንጻሩ ሁኔታዉን በጥርጣሪ ነዉ የሚመለከቱት።
«በጸጥታ እና የኢኮነሚ ጉዳዮች አንዳችን ከሌላችን ተለይተን መጓዝ የምንችል አይደለንም። ሁልግዜም ቢሆን ተባብረን ለነገሮች መንግድ እና መፍትሄ እናገኛለን። ያ ነዉ ዋንዉ ቁም ነገር»
ይህን ሲሉ የፖለቲካ ተንታኝዋ በሁለቱ አገሮች መካከል በፖለቲካም ሆነ በሌሎች ነገሮች ምን ግዜም ቢሆን ልዩነት መኖሩ አይቀርም ነዉ።
ክሪስቲና በርግማን/ አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ