1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደመራ በዓል አከባበር በርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ

ዓርብ፣ መስከረም 16 2012

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች የሚያከብሩት የደመራ በዓል ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ በሰላማዊና ኃይማኖታዊ ሥርዓት እየተከበረ መሆኑን የከተማይቱ ፖሊስ ዐስታወቀ። አዲስ አበባ የበዓሉ ሥፍራ የሚገኘው ወኪላችን እንደተመለከተው ከሆነ፦ ቀትር ላይ ባንዲራ የሚመስል የአንገት ልብስ ያደረጉ በዓል አክባሪዎችን ፖሊስ ሲከለክል ነበር።

Äthiopien Addis Abeba Vorabend der Meskele Feierlichkeiten
ምስል DW/S. Mushie

በሰላማዊና ኃይማኖታዊ ሥርዓት እየተከብሮአል

This browser does not support the audio element.

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች የሚያከብሩት የደመራ በዓል ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ በሰላማዊና ኃይማኖታዊ ሥርዓት እየተከበረ መሆኑን የከተማይቱ ፖሊስ ዐስታወቀ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፈይሳ በተለይ ለዶቸ ቬለ እንደገለጡት ፖሊስ አስቀድሞ ባደረገዉ ዝግጅት መሠረት በዓሉ ሥራዓቱን ጠብቆ እንዲከበር ከፍተኛ ክትትልና ጥበቃ እያደረገ ነዉ። የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ትናንት ባወጣዉ መግለጫ በኃይማኖት ጥያቄ ሽፋን በዓሉን ለማበጥና የተለያዩ የኃይማኖት ተከታዮችን ለማጋጨት የሚያሴሩ እንዳሉ ጠቁሞ ነበር። በአለተኛዉ በየበዓሉ ሥፍራዎች ግጭትን የሚቀሰቅሱ መልዕክቶች፣ አርማዎችና በሕገ-መንግሥቱ ከተፈቀደዉ ሰንደቅ ዓላማ ዉጪ ይዞ እንዳይወጣ ፖሊስ አግዶሏም። የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፈይሳ እንዳሉት አዲስ አበባ ዉስጥ ዛሬ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ፖሊስ የከለከላቸዉን ጽሑፎች፣ አርማና ባንዲራዎች ይዞ የወጣ በዓል አክባሪ የለም። አዲስ አበባ የበዓሉ ሥፍራ የሚገኘው ወኪላችን እንደተመለከተው ከሆነ፦ ቀትር ላይ ባንዲራ የሚመስል የአንገት ልብስ ያደረጉ በዓል አክባሪዎችን ፖሊስ ሲከለክል ነበር። የአዲስ አበባ ፖሊስ በዓሉ እንዳጀማመሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ከሰንበት ትምሕርት ቤቶች፣ ከበአሉ አዘጋጅ ኮሚቴና ከአብያተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር ተባብሮ እየሰራ ነዉ። የዘንድሮዉ የደመረ በዓል የሚከበረዉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በአብያተ ክርስቲያንና በምዕመናን ላይ ይደርሳል ያሉትን ጥቃት መንግስት እንዲያስቆም ባደባባይ ሰልፍ በሚጠይቁበት ወቅት ነዉ። የበዓሉን ድባብ በተመለከተ አዜብ ታደሰ ወደ አዲስ አበባ ወኪላችን ከሰለሞን ሙጬ ጋር ተወያይተናል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW