1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ

ሰኞ፣ መስከረም 16 2009

በመላዉ ኢትዮጵያ የመስቀል በዓል በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በነገው ዕለት  ይከበራል። ዛሬ በዋዜማው ደግሞ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የደመራ በዓል ስነ ስርዓት ተካሂዶዋል።

Meskel Feier in Awassa Äthiopien EINSCHRÄNKUNG
ምስል Hilina Photography

በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ዕለቱ በታላቅ ሀይማኖታዊ ሥርዓት የተከበረ ሲሆን፣ ችቦ በመለኮሱ ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርትያን ፓትርያርክ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፣ ዲፕሎማቶች እና የተጋበዙ እንግዶች፣ እንዲሁም፣ ምዕመናን  ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ መስከረም 16 ምዕመናን በተሰበሰቡበት በይፋ በአደባባይ የሚከበረዉ የዳመራ በዓል ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በመቀሌ ከተማም እየተከበረ እንደሆነ ወደ ስፍራዉ የተጓዘዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ገልጾልናል። ከሃይማኖት አባቶች በተጨማሪ፤ ተጋባዥ እንግዶች እና የመንግሥት ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን በከተማዋ በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ እጅግ ግዙፍ መስቀል የመትከል ዕቅድ መኖሩን ዘጋቢያችን ገልጾልናል። በአንፃሩ ለወትሮዉ የመስቀል እና የጥምቀት በዓል ደምቀዉ የሚከበሩባት ጎንደር የዘንድሮዉን የደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ሳይሆን በየአድባራቱ እንደምታከብር ነዉ ከስፍራዉ ያነጋገርናቸዉ የሃይማኖት አባት ከጎንደር መልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሚካኤል የገለጹልን።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ/ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW