1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የደሞዝና ሌሎች ጥያቄዎችን ያነሱ የትግራይ ሐይሎች የተቃውሞ ትዕይንት በመቀለ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሰኞ፣ ጥቅምት 3 2018

የደሞዝ እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያነሱ የትግራይ ሐይሎች አባላት ዛሬ በመቐለ የተቃውሞ ትዕይንት እያደረጉ ይገኛሉ። ዛሬ ረፋድ ጀምሮ ከከማው መሀል ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደውን መንገድ ጨምሮ በርካታ የመቐለ ከተማ ጎዳናዎች በእነዚህ ተቃውሞ እያሰሙ ባሉ የሠራዊት አባላት ተዘግተዋል።

የትግራይ ኃይሎች የተቃውሞ ትዕይንት በመቀለ
የደሞዝና ሌሎች ጥያቄዎችን ያነሱ የትግራይ ሐይሎች የመቀለን የተለያዩ መንገዶች ዘግተው ውለዋልምስል፦ Million Hailesillasssie/DW

የደሞዝና ሌሎች ጥያቄዎችን ያነሱ የትግራይ ሐይሎች የተቃውሞ ትዕይንት በመቀለ

This browser does not support the audio element.

 

ዛሬ ሰኞ ጠዋት እነዚህ የትግራይ ሐይሎች አባላት ከካምፖቸው በመነሳት በሰልፍ ወደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት እና ሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አምርተው የነበረ ሲሆን፥ በቦታው ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ አለማግኘታቸው ይናገራሉ። 

የሠራዊት አባላቱ የደሞዝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው፣ ተለይቶ ለቀድሞ የክልሉ ልዩ ሐይል የተሰጠ ድጎማ ለእነሱም እንዲሰጣቸው እንዲሁም የመኖርያ ቤት እና ሌሎች ድጋፎች እንዲመቻችላቸው ይጠይቃሉ።

እነዚህ የትግራይ ሐይሎች አባላት መንገዶችመዝጋታቸውን ተከትሎ በርካታ የሕዝብ መጓጓዣ አገልገሎት የሚሰጡ ታክሲዎች፣ የጭነት መኪኖች እንዲሁም ሌሎች ተሽከርካሪዎች ወደ ኩሓ በሚወስድ መስመር ቆመው ይታያሉ። የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣና ወዳሉበት መጥተው እንዲያነጋግሩዋቸው የሚጠይቁት እነዚህ የሠራዊቱ አባላት፥ ይህ ካልሆነ መንገዶቹ ተዘግተው እንደሚቆዩ ተናግረዋል። 

ሁኔታው ተከትሎ ከመቐለ አሉላ አባነጋ አየርመንገድ ጨምሮ በዛ መስመር ወደ መቐለ ማህል ከተማ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ተስተጓጉሎ ይገኛል።

ጉዳዮን አስመልክቶ ከክልሉ ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW