የደራሲዉ የብዕር ትግል
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 3 2005ማስታወቂያ
ታዋቂዉ ናይጀርያዊዉ ደራሲና የፖለቲካ ሃያሲ ቺኑአ አቼቤ በጎ,አ 2002 ዓ,ም ጀርመንን በጎበኘበት ወቅት አዉሮጳዉያን ስለአፍሪቃ የሚያስቡትና የሰሙትን ስር የሰደደ ትክክለኛ ያልሆነን አመለካከት እንዲቀየሩ ባደረገዉ ንግግር እንዲህ ሲል አሳስቦ ነበር።
ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በስነ-ጽሑፍ ስራዉ በዓለም አድናቆትን ያገኘዉ ናይጀሪያዊ ደራሲ ፕሮፊሰር ቺኑአ አቼቤ በ82 ዓመቱ ባለፈዉ ሰምወን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይትዋል። ደራሲዉ በስነ ጽሁፍ ስራዎቹ ብቻ ሳይሆን የሚታወቀዉ በጋዜጠኝነት አስተማሪነት እና በጠንካራ ሃያሲነቱም ነበር። የናጀርያዊዉ ደራሲ ቺኑአ አቼቤ የስነ-ጽሁፍ ስራዎች በዓለም አገራት ቋንቋዎች ተተርጉመዉ በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለስነ-ጽሁፍ ማስተማርያነትም ጥቅም ላይ ዉለዋል። በዕለቱ ዝግጅታችን የፕሮፊሰር ቺኑአ አቼቤን ስራዎች እናያለን የሀገራችንን የስነ-ጽሁፍ ይዘት የሚነግሩንን ምሁራን ጋብዘናል
አዜብ ታደሰ