የደቡብ አፍሪቃ ፖለቲካ
ረቡዕ፣ ግንቦት 10 2008ማስታወቂያ
በትናንትናዉ ዕለት የሀገሪቱ ምክር ቤት አባላት የእሳቸዉን ዘገባ ወይም ንግግር ላለመስማት ያሳዩት ተቃዉሞ የኃይል ርምጃን ሳይቀር አስከትሎ ታይቷል። ምክር ቤቱ ዉስጥ ቀይ ልብስ ለብሰዉ የሚታደሙት ለኤኮኖሚ ፍትህ እታገላለሁ የሚለዉ ፓርቲ አባላት ያሳዩትን ተቃዉሞ ለማስቆም የጸጥታ ኃይሎች የተከበረዉን የሕብ ተወካዮች መሰብሰቢያ አዳራሽ የድብድብ መድረክ አስመስሎታል። የሀገሪቱ ቴሌቪዥኖች በቀጥታ ያሰራጩት ይህ ትዕይንትም የደቡብ አፍሪቃ ፖለቲካ ወዴት እያመራ ነዉ የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ሸዋዬ ለገሠ ይህን በሚመለከት ከጆሃንስበርግ ጋዜጠኛ መላኩ አየለን በስልክ አነጋግራለች።
መላኩ አየለ
ሸዋዬ ለገሠ