ጉባኤዉ ክሊንተንን በይፋ ሰይሟል
ሐሙስ፣ ሐምሌ 21 2008ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባኤ የሐገሪቱን የቀድሞ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ወይዘሮ ሒላሪ ክሊንተንን የፓርቲዉ እጩ ፕሬዝደንት አድርጎ በይፋ መረጠ። ፊላደልፊያ-ፔንሲልቬንያ የተሰየመዉ የፓርቲዉ ጉባኤ የክሊንተንን እጩነት ካፀደቀ በኋላ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ የተያዩ ታዋቂ ፖለቲከኞች ለእጩዋ ያላቸዉን ድጋፍ በንግግር ገልፀዋል። ከጉባኤዉ አዳራሽ ዉጪ ግን የወይዘሮ ክሊንተንን መርሕ የሚቃወሙ ወገኖች ተሠልፈዉ ክሊንተንን አዉግዘዋል። ባለፈዉ ሰኞ የተጀመረዉ የዲሞክራቶቹ ፓርቲ ጉባኤ ዛሬ የክሊንተንን ንግግር ካደመጠ በኋላ ይጠናቀቃል። የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ