ዲጂታል ዓለምአፍሪቃ
የዲጂታል ግንዛቤ “ሌሎቹ ብልሆች” ድራማ
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 12 2017
ማስታወቂያ
ጀምበሬ፣ ራሒም እና እምነት ሌሎቹ ብልሆች በተሰኘው በዚህ ተከታታይ የራዲዮ ድራማ ከአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ (ሰው ሠራሽ አስተውሎት) ጋር ይተዋወቃሉ። በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሠማሩት ሦስቱ የኢንዙና ነዋሪዎች ስለ ቴክኖሎጂው ያላቸው ግንዛቤ በጣም የተለያየ ነው።
በማኅበራዊ ድረ-ገጾች በምታቀርባቸው ዝግጅቶች እና በተጽዕኖ ፈጣሪነት በምታገኘው ገቢ የምትተዳደረው ጀምበሬ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርት የሆነችው እምነት ከቴክኖሎጂው ጋር የሚተዋወቁት በራሒም በኩል ነው።
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆነው ራሒም አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ከለት ተለት የቤት ውስጥ ሥራዎች እስከ ሕይወት አድን ጥረቶች ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ያምናል። ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም የሚያደርገው ሙከራ ግን ለአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ገና በቅጡ ካልተዘጋጀችው ኢንዙና ሕግ እና ከባለሥልጣናቱ ጋር ያጋጨዋል።
ደራሲ፦ ጄምስ ሙሐንዶ
ተርጓሚ፦ እሸቴ በቀለ
ፕሮዲውሰር ፦ ልደት አበበ እና ሐና ደምሴ