ዲጂታል ዓለምአፍሪቃ
የዲጂታል ግንዛቤ “የኔ ፍቅር 4.0” ድራማ
እሑድ፣ ሐምሌ 6 2017
ማስታወቂያ
ይህ “የኔ ፍቅር 4.0” የተሰኘው አዲስ እና ባለ 10 ክፍል የዶቸ ቬለ በማድመጥ መማር ድራማ ነው። በዲጂታል መተግባሪያዎች ላይ የሚያተኩረው የዚህ ድራማ ደራሲ ኡርሲል ኙዌ ይባላል። ታሪኩ በሚከናወንበት ኢንዙና ከተማ አንድ አፓርታማ ውስጥ የሚኖሩትን ሶስት የወንድማማች ልጆች ጀምበሬ፣ እምነት እና ራሒምን መልሰን እናገኛቸዋለን።
እምነት ሥራ የሚበዛበት እና በኢንተርኔት የምትማረክ መምህርት ናት። ራሒም የኮምፒዩተር ባለሙያ ሲሆን በማህበራዊ ኑሮው በጣም ግራ የሚያጋባ ነው። በአንፃሩ ጀምበሬ ግልፅ እና ተግባቢ ናት። በነፃ መንፈስ ለማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች ታቀርባለች።
ደራሲ፦ ኡርሲል ኙዌ
ተርጓሚ፦ ልደት አበበ
ፕሮዲውሰር ፦ ልደት አበበ እና ሐና ደምሴ