ዲጂታል ዓለምአፍሪቃ
የዲጂታል ግንዛቤ “ዲጂታል መፍትሔዎች” ድራማ
ቅዳሜ፣ ግንቦት 16 2017
ማስታወቂያ
ዲጂታል መፍትሔዎች በተሰኘው ታሪክ ኢንዙና በተሰኘችው ምናባዊ የአፍሪቃ ከተማ አንድ ላይ የሚኖሩትን የሶስት ወንድማማች ልጆች እምነት ፣ ጀምበሬ እና ራሒምን መልሰን እናገኛቸዋለን። በከተማዋ ውስጥ ቤት ለመከራየት እጅጉን ውድ ከመሆኑ የተነሳ የቤት ኪራይ ዋጋውን ለመጋራት እና ወጪ ለመቆጠብ ሲሉ ዘመዳሞቹ አንድ አፓርታማ በጋራ ተከራይተው ይኖራሉ።
ሶስቱ ወጣቶች ምንም እንኳ ዘመዳሞች ቢሆኑም በጣም የተለያየ ፍላጎት እና አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው። ጀምበሬ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆና ስትሰራ የራሷን ነጻነት መጎናጸፍ የቻለች እና መንፈሰ ጠንካራ ናት።
ራሒም የበለጠ አስተዋይ ወጣት ቢሆንም ትክረቱ ያለው በኮምፒዉተሩ ላይ ብቻ ነው ። ነገር ግን ከኒና ጋር ያለው የፍቅር ግንኙነት የበለጠ ተግባቢ እንዲሆን አድርጎታል። እምነት ቁርጠኛ፣ ኃላፊነት የሚሰማት መምህርት ስትሆን ለኢንተርኔት ያላት ጉጉት ወሰን የለውም።
ደራሲ፦ አንድሪያ ዎግኒን
ተርጓሚ፦ ታምራት ዲንሳ
ፕሮዲውሰር ፦ ልደት አበበ እና ሐና ደምሴ