የድሬደዋ ሀረር እና ጅጅጋ ነዋሪዎች የአዲስ አመት ምኞት
ሐሙስ፣ መስከረም 1 2018
ባሳላፍነው ዓመት ከሀገሪቱ አካባቢዎች በአንፃሩ የነበረው ሰላም ሰዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ያስቻለ መሆኑን አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የድሬደዋ ፣ ሀረር እና ጅግጅጋ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ዓመቱ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በነበረው የሰላም መደፍረስ ሳቢያ ኢኮኖሚያዊ ጫና ማስከተሉም ተጠቅሷል።
አዲሱ አመት ካለፈው የተሻለ ሰላም የሚሰፍንበት እንዲህም አስተያየት ሰጭዎች ምኞታቸውን ገልፀዋል።የድሬደዋ ነዋሪው አቶ ወንደሰን ዘለቀ በድሬደዋ አንፃራዊ ሰላም እንደነበር በማንሳት" ወጥተን ለመግባት ሰላም ወሳኝ ነው" ብለዋል።መጪው አዲስ አመት ካለፈው የበለጠ የሰላም ፣የፍቅር እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።
ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች አንፃር በምስራቅ ሀገሪቱ ክፍል የተሻለ ሰላም ቢኖርም ኢኮኖሚያዊ ችግር ነበር ያሉትየሀረር ከተማ ነዋሪው አቶ ቶማስ በበኩላቸው የታጠቁ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ ከመንግስት ጋር ቢቀራረቡ ለሀገራችን ጠቃሚ መሆኑን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የጅግጅጋ ተወላጇ ወ/ሮ መቅደስ ኃይሉ በሶማሌ ክልል ሰላም በመሆኑ ልማት ማካሄድ መቻሉን ጠቁመዋል .ወ/ሮ መቅደስ በአዲሱ አመት ቀድሞ የነበረው ፍቅራችን፣ አብሮነታችን የበለጠ ጠንክሮ ጥሩ ነገር የምናይበት ይሁን ሲሉ ተመኝተዋል።
ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
መሳይ ተክሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ