1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድርድር ጥሪ

ሐሙስ፣ ግንቦት 17 2015

በአካባቢአቸው አሁንም የተዘጉ መንገዶች አለመከፈታቸውን፣ ሰብአዊ ድጋፍ እየደረሳቸው እንዳልሆነ እንዲሁም ለተሻለ ህክምና ወደ ሌላ ከተማ መሄድ አንችልም ብለዋል፡፡ ሁለቱ ሀይሎች በጦርነት ልዩነታቻውን ከመፍታት ይልቅም ህዝቡን በማይጎዳ መልኩ በውይይት በመፍታት መንግስት ተፈናቅው የነበሩ ሰዎችም ወደ የቤታቸው እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Äthiopien | Binnenvertrieben aus Oromia
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

የወለጋ ዞኖች ነዋሪዎች ሥጋትና ጥያቄ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ መንግስትና መንግስት ኦነግ ሸኔ በሚል ስም በአሸባሪነት የፈረጀዉ ነገር ግን ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) ብሎ የሚጠራዉ ቡድን ያቋረጡትን የሰላም ድርድር እንዲቀጥሉ በሁለቱ ወገኖች ዉጊያ የተጎዱት አካባቢዎች ነዋሪዎች ጠየቁ።የኢትዮጵያ መንግስትና የኦነሰ ተወካዮች ባለፈዉ ሚያዚያ አጋማሽ ዛንዚባር-ታንዛኒያ ዉስጥ የጀመሩትን ድርድር ለመቀጠል መስማማታቸዉን አስታዉቀዉ ነበር።ይሁንና ድርድሩ ከቀጠሮ ሌላ ያለዉጤት ማብቃቱ ከተነገረ ወዲሕ የሁለቱ ወገኖች ኃይላት በየአካባቢዉ እየተጋጩ ነዉ,።ተደጋጋሚ ግጭት የሚደረግባቸዉ የተለያዩ የወለጋ ዞኖች ነዋሪዎች እንዳሉት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሁለቱ ወገኖች ድርድር መቀጠል አለበት።

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ባይሳ ተፈራ በአካባቢአቸው አሁንም የተዘጉ መንገዶች አለመከፈታቸውን፣ ሰብአዊ ድጋፍ እየደረሳቸው እንዳልሆነ እንዲሁም ለተሻለ ህክምና ወደ ሌላ ከተማ መሄድ አንችልም ብለዋል፡፡ ሁለቱ ሀይሎች በጦርነት ልዩነታቻውን ከመፍታት ይልቅም ህዝቡን በማይጎዳ መልኩ በውይይት በመፍታት መንግስት ተፈናቅው የነበሩ ሰዎችም ወደ የቤታቸው እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡ 
በምዕራብ ወለጋ ግምቢ ከተማ እንደሚገኙ እና ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ ሰሜ አይጠቀስ ያሉ ነዋሪም በሚኖሩበት ስፍራ በነበረው ግጭት ሳቢያ የተወሰኑ የበተሰባቸው አባላት ወደ ደብረ ብርሀን ከተማ ሸሽተው እንዳሉ ነግረውናል፡፡ በመንግስት እና ታጣቂዎች መካከል ተጀመርው የነበረው ድርድር ተሳክቶ በአካባቢው ሰላም ቢሰፍን በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ከተፈናቀሉበት ከጊምብ ከተማ በቅርብ ርቅት ላይ በሚትገኘው ቶሌ የተባለች ቀበሌ እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡ በተሰቦቻቸውን ጨምሮ የሸሹ ዘመዶቻቸው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡
የሆሮ ጉደሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ  ነዋሪ የሆኑት አቶ መሀመድ ኢስማኤም በበኩላቸው ለዓመታት በቆየው የጸጥታ ችግር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በወረዳው ሁለት ቀበሌ ውስጥ የነበሩት ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ደግሞ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ጠቁመዋል፡፡ በመንግስትና ታጣቂዎች መካከል በሚከሰቱት ግጭቶችም ሆነ በተለያዩ ስም የሚንቀሰቃሱ ታጣቂዎች በሚያደርሰው ድንገተኛ ጥቃት  በሚሊዩን የሚገመት ንብረት ወድመዋል ብሏል፡፡ ግጭት ለማቆም ተጀምሮ የነበረው ድርድር ተፈጻሚ ይሆናል በማለት እየተከታሉ እንደሚገኙም አብራርተዋል፡፡ 
የምዕራብ ኦሮሚያን ጨምሮ በተለያዩ ስፍራዎች የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት በታንዛኒያ ተጀምሮ የነበረው ውይይት እንድቀጥልና ዘላቂ ሰላም ይሰፍን የሚል ሀሳብ በተደጋጋሚ እየቀረበ ይገኛል፡፡ በወለጋ ዞኖች ብቻ በግጭቶች ምክንያት 7 መቶ ሺ ሰዎች ተፈናቅለው እንደነበር ከዚህ ቀደም የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዩች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መረጃን ዋቢ አድርገን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ የምስራቅ ወለጋ ዞን ደግሞ ከዚህ ቀደም ከ2 መቶ ሺ በላይ ሰዎች  ተፈናቅለው  እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በኦሮሚያዉ ግጭት የተፈናቀሉምስል Alemnew Mekonnen/DW

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW